አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ
ሐሙስ፤ ግንቦት ፲፫ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 5/21/2015 )

“ሕዝብን ነፃ የሚያወጣው፤ ራሱ ሕዝቡ ነው።” ዶክተር መሳይ ከበደ
“ሰላማዊ ትግሉ ነው መንግሥትን የሚያንበረክከው።” ዶክተር መሳይ ከበደ

ኢሳት ይኼን ዝግጅት አቅርቦ፤ በቪዲዮ ሌሎቻችን እንድናየው በማድረጉ፤ ከፍተኛ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ቀጥሎም ይህ ርዕስ፤ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ፤ ለዚሁ ላደረጋችሁት ጥረት፤ ደግሜ እንዳመሰግናችሁ ይፈቀድልኝ። የነበረው ዝግጅት፤ በኔ ግምት፤ ምን እንደሆነ መላ እጥልና፤ ዝግጅቱ በአንድ ምክንያት ወይንም በሌላ፤ የጎደለው አለ ብዬ ያመንኩበትን፤ ማሟያ ይሆን ዘንድ፤ ይኼው አቅርቤያለሁ።
በመሠረቱ እኔ ሳየው፤ ይህ ዝግጅት፤ በቦታው በሌለው የትግል ማዕከል ላይ፤ መንደርደሪያ ሃሳብ ለመሥጠት የተደረገ ነው ነው የምለው። ትግላችን ማዕከል የለውም። መቶ በመቶ ትክክል። ማዕከል የሌለው ለምንድን ነው? ጥሩ ጥያቄ። ማዕከል የሚመሠረተው፤ በታጋዮቹ መካከል ባለው ሀቅና የግንዛቤ ስምምነት ላይ የተመሠረተ አንድነት ሲኖር ነው። በኔ እምነት፤ በዝግጅቱ የነበሩት ሁሉም እንዳቀረቡት ሁሉ፤ ለማዕከሉ መኖር አለመኖር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ቅንጣት ታክል አስተዋፅዖ የለውም። ስለዚህ ጉድለቱ ከኛው ነው። ዶከተር ብርሃኑ እዚህ ላይ ጥሩ ነጥብ አስቀምጧል። “መሠረታዊ የሆነ ችግር በመካከላችን አለ!” በማለት። ላለመተባበራችን ደግሞ፤ “መተማመን በመካከላችን መጥፋቱ ነው!” በማለት አስቀምጧል። ታዲያ መተማመን ለመጥፋቱ መሠረቱ ምንድን ነው? ለኔ፤ አንድ ላለመሆናችን ዋናው ምክንያት፤ አንድ የሆነ የትግል አመለካከት ስለሌለን ነው። የሰላማዊ ትግል ወይንም የትጥቅ ትግል ለሚለው “ምርጫ” መልስ ስላልሠጠነው ሳይሆን፤ ወይንም ከሰላማዊ ትግሉ ወይንም ከትጥቅ ትግሉ አንዱን መምረጥ ስላልቻልን ሳይሆን፤ ባጠቃላይ ትግሉ የተበታተነ አመለካከት ስላለን ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ፤ በትግሉ ምንነት ላይ ያለን አመለካከት፣ በትግሉ ሂደትና ከትግሉ በኋላ መከተል ስላለበት ሥርዓት፤ የመልስ አንድነት ስለሌለን ነው።
ይህ የኢሳት ዝግጅት፤ የትግሉ ማዕከል ሆኖ አሽከርካሪነቱን መውሰድ ያለበት፤ ሰላማዊ ትግል ነው ወይንስ የትጥቅ ትግል? የሚለውን ለመመለስ የተደረገ ይመስላል። ከሆነም ጥሩ ነው። አይደለም ከተባለ፤ ለኔ የሠጠኝ ትርጉም ይሄ ነው። እናም፤ “የትጥቅ ትግሉ ብቸኛ አማራጭ ነው! ሰላማዊ ትግሉ አይሠራም! እናም የትግሉ ማዕከል የትጥቅ ትግሉ መሆን አለበት!” ተብሎ በዝግጅቱ ተደምድሟል። በዚህ ላይ ከሰማይ የራቀ ልዩነት አለኝ። በኔ እምነት፤ አሁንም ማዕከሉ የሰላማዊ ትግሉ ነው። አሁንም ማዕከሉ የሀገር ቤቱ ሕዝባዊ መነሳሳት ነው። ዶክተር መሳይ ከበደ፤ እግረ መንገዳቸውን ይሄኑ አስቀምጠውታል። በርግጥ መልሰው አይሆንም ያሉበት አለ፤ በዚያ ላይ እመለስበታለሁ። በምኞት መጋለብ ጥሩ ነው። በምኞት ጋልቦ በእውን ካሰቡት ለመድረስ መሞከር፤ በቀላሉ ሲታይ የዋህነት፤ ከዚያ ከተለየ ደግሞ ማጭበርበሪያ ጮሌነት ነው። ለኔ ይህ ዝግጅት፤ ሌላውን ክፍል አለማካተቱ ብቻ ሳይሆን፤ ሀቅነት በጎደለው መልክ፤ የሰላማዊ ትግሉን ሚና ብዥታ በተሞላበት መንገድ በማቅረቡ፤ እኒህን ብዥታዎች ግልጽ ማድረጉ፤ ግዴታዬ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በሂደት አሳያለሁ።
ወደ ዝግጅቱ እንመለስ። ዝግጅቱ ርዕስ ተሠጥቶት የቀረበና አቅጣጫ ያለው በመሆኑ፤ ከርዕሱ ልጀምር። እንዲህ ይላል፤

በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ፣ የልማት የወደፊት ዕድል እና መረጋጋት ላይ የተካሄደ ስብሰባ ክፍል ፩
እምኑ ላይ ነው ከኢትዮጵያ ወጥቶ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የተወያየው? ርዕሱና ይዘቱ ለምን አልተገናኙም? ወይንስ ኢሳያስ አፈወርቂን ለማስደሰት የተደረገ የርዕስ ማሸጋሸጊያ ነው? “የአፍሪካ ቀንድ” የተባለበት፤ አንተንም አንስተንሃል ለማለት ነው!
አቶ ኤርምያስ ለገሰ ያቀረበው በጣም ጠቃሚ ነበር። ገዥው መንግሥት እያደረገ ያለውን ሀቅ፤ በትክክል አስቀምጦታል። የጎደለው አለ ለማለት፤ ከአቶ ኤርምስ የበለጠ ካድሬ ሆኖ ለገዥው መንግሥት ማገልገልን ይጠይቃልና፤ የለሁበትም። ይልቁንስ ከዚህ ተነስቶ፤ የስትራተጂ ሳይሆን፤ የታክቲክ መሸጋሸጎችን በማድረግ፤ የሰላማዊ ትግሉን ማጠናከር ይቻላል።
እስኪ ከተነገሩት ውስጥ የጎሉ የሰላማዊ ትግል ብዥታዎችን እንጎብኝ፤

ብዥታ ፩. በኃይል የመጣ ባለሥልጣን፤ በኃይል መወገድ አለበት። ( ዶክተር ጌታቸው በጋሻው )
ዶክተር ጌታቸው ይኼን በሙሉ ልቡ ሲናገር፤ ክብደት ሠጥቶ አጢኖታል ማለት ይቸግረኛል። ታዲያ በዚህ አዙሪት ስንሽከረከር እንድንኖር ነው እንዴ፤ እንታጠቅ የሚል መልዕክት ያስተላለፈው? በኃይል የመጣው ሁሉ፤ የግድ በኃይል መወገድ ካለበት፤ መቸ ነው ሰላማዊ መንግሥት የሚኖረን? በኃይል ማስወገድ ያለብን፤ “ያለው ገዥ ቡድን በኃይል ስለመጣ ነው!” የሚለው ቁንጽል ነው። የትጥቅ ትግልን እንዳማራጭ ለማቅረብ፤ ጠለቅ ያለ ትንተናና መሠረታዊ ግንዛቤን ይጠይቃል። በምን ሁኔታ ላይ በተግባር መዋል አለበት? የሚለው ደግሞ ራሱን የቻለ ርዕስ ነው። እዚህ ላይ፤ አፌን ሞልቼ፤ ዶክተር ጌታቸው በጋሻው ተሳስቷል እላለሁ።
ምክንያቴ፤ በኃይል የመጣ ሁሉ መጥፎ አይደለም። መጥፎነት፤ ከአመጣጥ ሳይሆን ከመጪው ተግባር ይቀዳል። ከዚህ ተግባሩ ተነስቶ ነው አወጋገዱም መተለም ያለበት። ያም ሲሆን ደግሞ፤ መቼና እንዴት ሊሆን እንደሚችል ራሱን የቻለ የተለዬ የራሱ የቦታው ጥናትን ይጠይቃል። አንድ ጥብቆ ለሁሉም የሚገጥም አይደለም።

ብዥታ ፪. መንግሥቱ ለሰላማዊ ትግሉ አመቺ ሆኖ መገኘት አለበት። ሰላማዊ ትግል ማለት፤ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፤ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሆኖ ሲገኝ የሚካሄድ የትግል ስልት ነው። ( ዶክተር መሳይ ከበደ )
በማንኛውም ሀገር ቢሆን፤ “እኔን ለመገልበጥ፤ ሰላማዊ ትግል እንድታደርጉ እፈቅድላችኋለሁ!” ያለ መንግሥት አልተመዘገበም። አይኖርምም። ሰላማዊ ትግል፤ በገዥው ውዴታ የሚካሄድ ሳይሆን፤ ያለገዥው ውዴታ የሚካሄድ ነው። የመስዋዕቱ ክፍያ፣ ለመሪዎቹ የሚያጋጥመው ፈተና፣ የሚጠይቀው የሕዝቡ ቆራጥነት፤ ደረጃው የተለያየ ይሆናል። አማራጮቹ ጠበው፤ ሕዝቡ አንድነት ሆኖ፤ በር አስከፋችና ጫና ሠጪ አንድ ረዳት የታጠቀ ድርጅት ሲኖር፤ ሰላማዊ ትግሉ በደበዘዘ መንገድ ይቀጥላል እንጂ፤ አይሠራም የሚለው፤ ከጀርባው ያለው መጠናት አለበት።

ብዥታ ፫. ሰላማዊ ትግሉ እስካሁን ውጤት ስላላስገኘ፤ ወደፊትም አያስገኝም። ( ዶክተር መሳይ ከበደ )
ሰላማዊ ትግሉ ጥንካሬ ሊገዛና ስኬት ሊያስከትል እንደሚችለው ሁሉ፤ እንደመሪዎቹና እንደ የተለዬ የቦታው ተጨባጭ ሀቅ፤ ሊሰናከል ይችላል። ሰላማዊ ትግሉ ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጠው፤ ሲሳካ ከሆነ፤ መቼ ነው የሚጀመረው? ምክንያቱም ስላልተሳካ ወደፊትም አይሳካም የሚል ቀንድ በራሱ ላይ ተጭኗልና! እናም ዶክተር መሳይ ተሳስተዋል።

ብዥታ ፬. የማይቻል ነገርን ( ሰላማዊ ትግልን ) እንዳማራጭ ማቅረብ ትክክል አይደለም። ( ዶክተር መሳይ ከበደ )
የማይቻል ተብሎ መፈረድ ያለበት ምኑና መቼ ነው? ሰላማዊ ትግል አይቻልም ስንል፤ ምን ማለታችን ነው? ሰላማዊ ትግል ጠርዞቹ የት ላይ ናቸው? ተማሪዎቹ አንድ የገዥው ካድሬ በሚያደርግባቸው በደል፤ ለአንድ ቀን ትምህርት እናቆማለን ቢሉ፤ የለም አይቻልም ልንል ነው? ሠራተኞች በአላሙዲ የወርቅ መጋዝን “ደሞዛችንን አዘገዩብን! ልንሞት ነው!” ብለው ቢያምጹ፤ የለም አትነሱ፤ ትክክለኛ አማራጭ አይደለም ልንላቸው ነው? የሰላማዊ ትግል ግንዛቤያችን ምንድን ነው? የማይቻል ነው ስንል፤ ምን ማለታችን ነው? ሰላማዊ ትግል ምን ጊዜም አማራጭና መወስድ ያለበት የትግል ዘዴ ነው። ጥልቀቱ፣ መቼና እንዴት በተግባር ላይ መዋል እንዳለበት፤ በቦታውና በታጋዩ ጥንካሬ የሚወሰን ይሆናል። አይቻልም የሚለው የኢትዮጵያ ሰላማዊ ታጋዮችን ጥረት ካለመገንዘብ የመጣ ነው። ተችሎማ ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈሉ እየታገሉ ናቸው። መስተካከል ያለበት ጉዳይ አለ ማለት ሌላ ነው። በዚያ እስማማለሁ። ያን ለማለት የተወረወረ ከሆነ፤ አጋራቸዋለሁ። ትክክል አይደለም ማለት ግን የተለየ ነው።

ብዥታ ፭. ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል የግድ መነጋገር የለባቸውም። ውጤታቸው ነው መዳመር ያለበት። ( ዶክተር መሳይ ከበደ )
እዚህ ላይ ከዶክተር መሳይ ከበደ ጋር መሠረታዊ ልዩነት አለኝ። ሁለት የተለያዩ ድርጅቶች፣ ሁለት የተለዩ የትግል ስልቶች፣ . . . አሁን ባሉበት ሁኔታ ያልተነጋገሩና አብረው ያልዶለቱ፤ ሥልጣን በመካፈሉ ወቅት ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ማለት፤ በተለይ አንዱ ታጥቆ ሌላው በባዶው፤ በቀላሉ ቅዠት ነው። እስኪ ታጥቀው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አዲስ አበባ ሲገቡ የተከተለውን እናጢን! ወይንስ ከቅርብ ታሪካችን መማር አንችልም? እዚህ ላይ ዶክተር መሳይ ከበደ በግልጽ ተሳስተዋል።

ብዥታ ፮. በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፤ ሰላማዊ ትግል የማይፈቅድ ከሆነ፤ ሰላማዊ ትግል አይሠራም። ( ዶክተር ብርሃኑ ነጋ )
ይኼ በቁጥር አንድ ስለተመለሰ፤ አልደርትበትም።
ዶክተር መሳይ ከበደ በሰላማዊ ትግሉና በትጥቅ ትግሉ መካከል “የራሳቸው” የሆነ ጎዳና መፈለጋቸው ግልጽ ነው። ትግሉን ይፈልጋሉ። ውጤታማ እንዲሆን ይሻሉ። በተጨማሪ ደግሞ፤ ሁለቱም በተለያዩ ክፍሎች የተያዙ በመሆናቸው፤ እኒህን ክፍሎች የትግሉ አካል አድርገው ማቅረብ ይፈልጋሉ። ሁለቱን ወገን አራማጆቹን በርቱ ሊሉ ይፈልጋሉ። እዚህ ላይ ነው፤ ከሁሉም ለመሆን የሚያደርጉት ጥረት የሚታየው። አላዛለቃቸውም።
“የማቀርበው የግል አመለካከቴን ነው።” በማለት የሚጀምረው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፤ በትክክል ችግር እንዳለብን ገልጿል። በሱ እምነት የችግሩ ምንጭ ያለውን አቅርቧል። በ “ዘውግ” – የሱ ቃል ነው – የተደራጁትን ለምን ማምጣት እንደፈለገ ለኔ ግልጽ አይደለም። “ከኢትዮጵያ ነፃ መውጣት እፈልጋለሁ።” ብሎ፤ ጦሩን አደራጅቶ የተሰልፈን ክፍል፤ “የለም ከኢትዮጵያ ነፃ አትወጣም። እኔ በምነግርህ ትሰባሰባለህ።” ማለት፤ ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ “ላንተ የማውቅልህ እኔ ነኝ!” የሚል እብሪት ይሆናል። ቀጥሎ ደግሞ፤ “አንተ ኢትዮጵያ አይደለሁም ብትልም፤ እኔ ኢትዮጵያዊ ነህ ብየሃለሁ!” የሚል ሌላ እብሪት ነው። ታዲያ እንዴት ተብሎ ነው፤ በነዚህ ድርጅቶችና በኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች መካከል መተማመን የሚፈጠረው? “ኢትዮጵያዊ ነኝ!” እና “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም!” የሚለው ወሳኝ ጥያቄ፤ በመተማመን ተፈቶ በአንድነት ሊሠሩ ይችላሉ የሚለው፤ ግራ አጋብቶኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ፤ “ሌሎች ድርጅቶች ዴሞክራቶች ስላልሆኑ፤ በምርጫ ተማምነው ሳይሆን፤ በድርድር ሥልጣን ለማግኘት የተኮለኮሉ ናቸው!” እያለ ሌሎቹን እየፈረጀ፤ በሱ ድርጅትና በሌሎች ድርጅቶች መካከል መተማመን ይፈጠራል ብሎ ማለሙ፤ ለኔ ግራ የሚያገባ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
ምን ብናደርግ ነው ወደ ፊት ልንሄድ የምንችለው? መተማመን በመካከላችን ሲኖር ነው። መተማመን እንዴት ሊኖር ይችላል? ትግሉን ድል ካደረግን በኋላ ስለሚከተለው የፖለቲካ ችግር አሁን ከተስማማን፤ በቃ አለቀ። እንተማመናለን። ( ዶክተር ብርሃኑ ነጋ )
ይህ እውነት ነው? ለማን እየተናገረ ነው? የዚህ ትንታኔ ችግር፤ እንዴት በሥልጣን ላይ ያለውን ገዥ ቡድን እናቸንፈዋለን ሳይሆን፤ ሲቸነፍ ምን እንዲሆን እንስማማና ሁሉ ነገር አለቀ ማለቱ ላይ ነው። እዚህ ላይ፤ ገዥውን በማቸነፍ ሂደቱ ላይ የሚኖረው የኃይል አሰላለፍ ወሳኝ መሆኑን ይዘነጋል።
ባጠቃላይ የዚህ ዝግጅት ጉደለት ብየ የማቀርበው፤ ሰላማዊ ትግሉን ከሚደግፉ መካከልና፤ ባሁኑ ሰዓት የትጥቅ ትግሉ አደገኛ ነው! ከምንለው ክፍል፤ አብሮ አለማቅረቡ ነው። ለወደፊት ቢያደርጉት ጥሩ ነው።
ይህ ጽሑፍ በምንም መንገድ የትጥቅ ትግሉን በደፈናው የሚኮንን አይደለም። የትጥቅ ትግሉ የራሱ የሆነ ሁኔታ፤ ማለትም ቦታና ወቅት አለው። እንዲያው በጭፍን የሚወረወር አይደለም። የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፣ የታጋዩ ክፍል አደረጃጀት፣ ዓለም አቀፉ የፖለቲካ ሀቅና በገዥው ቡድንና በታጋዩ ሕዝብ መካከል ያለው የጉልበት ሚዛን ዝንባሌ ግድ ሲለው፤ አይቀሬ ይሆናል። ያኔም ቢሆን ግን፤ የትጥቅ ትግሉ፤ የሰላማዊ ትግሉ ረዳት በመሆን ነው የሚካሄደው። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉ፤ ወሳኝ በሆነ ሁኔታ የአመጽ ትግል ጠመንጃውን ይገዛዋል።

Source: Eske.mecha
No comments:
Post a Comment