Thursday, May 14, 2015

ሜሮን አለማየሁ ተፈቅዶላት የነበረውን ዋስትና ተከለከለች

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው ሜሮን አለማየሁ በፍርድ ቤት የተፈቀደላትን የዋስትና መብት ተከልክላ በእስር ላይ እንድትቆይ ተደርጋለች፡፡ ሜሮን ትናንት ሚያዝያ 5/2007 ዓ.ም ንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርባ ክስ የተመሰረተባት ሲሆን በ4000 ብር ዋስ ከእስር ተለቃ እንድትከራከር የዋስትና መብት ተከብሮላት ነበር፡፡
ይሁንና ሜሮንን በዋስትና ለማስወጣት ገንዘቡ በሲፒኦ ተይዞ የዋስትናው ጉዳይ ካለቀ በኋላ ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ የዋስትና መብቷን ከልክሎ በእስር እንድትቆይ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሜሮን ታስራበት ከነበረው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ ወደልታወቀ ቦታ ወስደዋታል፡፡
በተመሳሳይ በሰልፉ ምክንያት ተይዞ በ25 ሺህ ብር ዋስ ከወጣ በኋላ እንደገና ተይዞ በትናንትናው ዕለት 6 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጣ ከታዘዘ በኋላ እንደገና ዋስትናውን ተነጥቋል፡፡ ሜሮን አለማየሁና ዳዊት አስራደ ለተጨማሪ ምርመራ ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments: