የድሮ አያት አርበኞቻችን ከጠላት ጦር ጋር የተፋለሙትና የተዋደቁት ኃገራችን ኢትዮጵያ በጠላት እጅ እንዳትወድቅ ብቻ ሳይሆን ሰንደቃላማችን እንዳይወርድም ጭምር ነው። ለዚህም በባዶ እግራቸው የጠላት ጦርን በመደምሰስ በጣልያኖች የወረደዉ ሰንደቃላማችን መልሰው ከ5 ዓመት በኋላ በመስቀል ሃገራችንን አስከብረዋል። የተዋደቁለት ሰንደቃላማ ዛሬ ወያኔ ያመጣውን ኮከብ ያለበት ሳይሆን ከላይ ወደ ታች በአግድም አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ሲሆን ምንም አይነት ምልክት የለውም። ስለዚህ ዛሬ ወያኔ የሚጠቀምባት ባንዲራ ኢትዮጵያን ሊወክል አይችልም። በሌላ አነጋገር የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ወያኔ ኮከብ ያለበትን ከቀየረ ጊዜ ጀምሮ ስለወረደ አርበኞች አያቶቻችን የተዋደቁለት ሰንደቃላማ በወያኔ ተደፍሯል ማለት ነው። ስለዚህ እኛ ልጆቿ ታግለን ወያኔን በማስወገድ ሰንደቃላማችን በክብር ተሰቅሎ እንዲውለበለብ ማድረግ ይጠበቅብናል። ታድያ ሰንደቃላማችን ያዋረደው ወያኔ ስለየተኛው ሰንደቃላማ የተዋደቁትን አርበኞች ቀን ነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ የሚያከብረው?
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Seyoum Workneh
No comments:
Post a Comment