ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ሳይጀመርና ከሰልፉ በኋላ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በደህንነቶች ተደበደቡ፡፡
በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በትናንትናው ዕለት ቤታቸው የተበረበረ ሲሆን ዛሬ ሚያዝያ 23/2007 ዓ.ም በግዳጅ ‹‹የኢሜልና የፌስቡክ ፓስወርዳችሁን አምጡ!›› ተብለው አንሰጥም በማለታቸው መደብደባቸውን ገልጸዋል፡፡
ካሳንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ወይንሸት ሞላና ዳንኤል ተስፋዬ ‹‹የኢሜልና የፌስቡክ ፓስወርዳችሁን አምጡ!›› ተብለው አንሰጥም በማለታቸው ተደብድበዋል፡፡
ካሳንቺስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ወይንሸት ሞላና ዳንኤል ተስፋዬ ‹‹የኢሜልና የፌስቡክ ፓስወርዳችሁን አምጡ!›› ተብለው አንሰጥም በማለታቸው ተደብድበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment