ኢህአዴግ ከምርጫው በፊት ማን ሊመርጠው እንደሚችልና እንደማይችል ለማወቅ፣ እንዲሁም መራጮቹን ከአሁኑ ለመወሰን የ‹‹መራጮች ኔትወርክ›› የሚል ቡድን እያደራጀ መሆኑ ታወቀ፡፡ የመራጮች ኔትወርክ ብሎ የሚጠራውን ቡድን ለማቋቋም የየክፍለ ከተማው ደህንነቶች፣ ካቢኔዎች፣ የወረዳ ካቢኔዎች፣ የሴቶችና የወጣቶች ፎረሞች በሰፈርና በመስሪያ ቤት ፎርም እያዞሩ እያስሞሉ መሆኑን ታውቋል፡፡ በ‹‹መራጮች ኔትወርክ›› የተደራጁት ዜጎች ከአሁኑ ኢህአዴግን እንደሚመርጡ ቃል እንደሚገቡና ሌሎች ኢህአዴግን እንዲመርጡም የመመልመል ግዴታ እንዳለባቸውም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የእነዚህ የመራጮች ኔትዎርኮችን የሚመሩት የፓርቲ ካድሬዎች ሲሆኑ እነሱም በመራጮች ኔትወርክ ውስጥ የመራጮች ቡድን መሪና የቀጠና መሪ ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዱ ትዕዛዝ የሚመጣው ከማዕከላዊ የኢህአዴግ ጽ/ቤት እንደሆነም ታውቋል፡፡
No comments:
Post a Comment