Wednesday, June 10, 2015

ህወሓቶች በጽኑ አቋም የሚስማሙባቸው አጀንዳ ምን ምን ናቸው!??

አቶ ገብረመድህን አርአያ እንደዚህ አቅርቧቸዋል። ከህወሓት የተባበሩ አመራር የነበሩትም ሹማምንት በነዚህ ነጥቦች ላይ በጸና አቋም ይስማማሉ።
1. አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሕገመንግሥት የህወሓት ሕገመንግሥት ነው። ይህም ከ1967 እየታገልን ይዘነው የመጣን የሕይወታችን እና የንብረታችን መድን ነው። ይህ ሕገመንግሥት ከተናደ አሁን ያለነው የተባረሩት አመራርም ተለቅመን ታሰርን፣ ሃብታችን ተወረሶ እኛም እንገደላለን። ስለሆነም ያለውን ሕግመንግሥት መከላከል የግድ ይሆናል። ሁሉም በዚህ ይስማማሉ፡፡
2. ኢፈርት የህወሓት ሃብት ነው። ኢፈርትም በኢትዮጵያ ያሉትን ገዢ ተቋማት በተዘዋዋሪና በቀጥታ የሚቆጣጠር ነው። ለምሳሌ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ መአድናት፣ ትራንስፖርት ወዘተ. የሃገሪቱ ንግድም ከትንሹ እስከ ትልቁ የሚቆጣጠር ነው። ይህ የደም ስራችን ከወደመ በሕዝብ ቁጥጥር ከዋለ ህወሓትና መሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የህወሓት መንግሥታዊ ተቋማት ጭምር ይወድማሉ። ስለሆነም ባለን አቅማችን ኢፈርትን መከላከል በበለጠ ማሳደግ አለብን። በዚህም በማያወላውል መንገድ ይስማማሉ፡፡
3. የሕዝብ የአመጽ ተቃውሞ ወይም አብዮት ከተነሳ ባለን መከላከያ ሰራዊት ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ልንመልሰው አንችልም። ሕዝቡ ከአሸነፈ የህወሓት አመራር አባሎችና ደጋፊዎቻችንን በእሳት እንደሚቀቅለን እናውቃለን። ለዚህ መድሃኒቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በየጎሳ ከፋፍለን አሁን ባለው አይነት ደፍጥጠን ማጥቃት፣ ተቋዋሚ ድርጅቶችን ማዳከም፣ መግደል ማዋከብ አለብን። የአገዛዛችን መንገድ ሕዝቡን ማስጨነቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ በስደት እንዲጓዙ ማድረግ እነዚህን በዋናነት እንደ መሳሪያ መጠቀም አለብን። ወጣቱን ዜጋ ደግሞ በሽርሙጥና፣ ሃሺሽ ወዘተ. በብዛት አስፋፍቶ ከጥቅም ውጭ ማድረግ። በጎሳ ከፋፍለንም ኢትዮጵያዊነት የሚል ስር የሰደደውን እምነት ማጥፋት፣ የአማርኛ ቋንቋን ማጥፋት፣ በየትኛውም ጎሳ የሚገኘውን ስር መሰረቱን ነቅለን እንዳልነበረ ማድረግ። በዚህም ሁሉም ይስማማሉ።
ገብረምድህን አርአያ (አውስትራሊያ)

No comments: