Friday, December 5, 2014

በድጋሚ ሙሉ አዲስ አበባ ወረቀት አሸብርቃ አደረች።

አዲስ አበባ ውስጥ የ24 ሰዓቱ ሰልፍ ቅስቀሳና ወረቀት መበተን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ከነገ እስከ እሁድ ስለሚደረገው የ ሰዓት የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ መረጃ ደርሶታል። የወያኔ ጥበቃ ሃይሎች ሁለት የቀን በተደጋጋሚ ወረቀት ይበተናል ብለው ስላላሰቡ የእነሱ መዘናጋትን በመጠቀም የቅስቀሳው ግብረሃይል ለመቶ ሺህዎች በቂ የሆነ የወረቀት መበተን ስራ ሲሰሩ አድረዋል።
የመንግስት ባለስልጣኖች በፍርሃት ተጨናንቀዋል። በሃገራችን በደልና ምሬት በዝቷል። ድህነትና ጉስቁልና ከመቼውም በባሰ ተንሰራፍቷል። እስርና ሰቆቃ በደል በዝቷል። ለትግሉ የዲያስፖራ እገዛ እንደተጠበቀ ባይሆንም ህዝቡ ዓላማው ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንደማይል እየገለጸ ነው። 

ከተበተነው ወረቀት ፎቶ የተነሳ የቅስቀሳ ወረቀት


No comments: