Friday, December 12, 2014

የ5 አገራት ተወካዮች ከሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ መዋቅር ጋር ተወያዩ

የ5 አገራት ተወካዮች ከሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ መዋቅር ጋር በወቅታዊ የፖለቲካ ምህዳር፣ ገዥው ፓርቲ በሚወስዳቸው እርምጃዎችና በቀጣዩ ምርጫ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ አቶ ሉሉ መሰለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ 

ከጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ አየርላንድና ኦስትሪያ ተወካዮች ጋር በምርጫ ምህዳሩ፣ ገዥው ፓርቲ በሚያደርሳቸው ጫናዎች፣ የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ፣ ፖሊሲዎችና አቅም ላይ ሰፋ ያለ ውይይት እንዳደረጉ ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

ከአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች መካከል በፍቃዱ አበበ በ‹‹ሽብርተኝነት›› ተከሶ ለአራት ወር ያህል ማዕከላዊ ቆይቶ አሁን ወደ ቂሊንጦ መዛወሩ የሚታወቅ ሲሆን በዞኑ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅርም ከፍተኛ ወከባ እየተደረገበት እንደሚገኝ ተገልጹዋል፡፡

በጋሞጎፋ ዞን የሚንቀሳቀሱ የሰማያዊ አባላት በገዥው ፓርቲ የሚደርስባቸው ጫና ከፍተኛ መሆኑንና ይህም ምህዳሩ እንዲዘጋ እንዳደረገ፤ ይህ የተዘጋ ምህዳር በምርጫ ለመሳተፍ የማያስችል መሆኑን፣ ነገር ግን ገዥው ፓርቲ ምህዳሩ እንዲሰፋ የበኩሉን አስተዋጸኦ ከተወጣ በሁሉም ወረዳዎች የማሸነፍ አቅም እንዳላቸው ለተወካዮቹ ማስረዳታቸውን አቶ ሉሉ መሰለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

No comments: