Wednesday, December 3, 2014

ከ3 ወር በፊት የታፈነው የመኢአድ አመራር የት እንደደረሰ አልታወቀም

• የሶስቱ ፓርቲዎች አመራሮች ለታህሳስ 21/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል

የገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ከየ ክፍለ ሀገሩ ማሰር በጀመሩበት ወቅት በደህንነትና ፖሊሶች የታፈነው የመኢአድ አመራር የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የሰሜን ጎንደር አመራር የሆነው አቶ ችሎት ባዜ መስከረም 2/2007 ዓ.ም በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች የታፈነ ሲሆን በወቅቱ ቤተሰቦቹ ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንደተዛወረ መረጃ ደርሷቸው እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም በተደጋጋሚ አቶ ችሎት ወደ ማዕከላዊ መዛወር አለመዛወሩን ቢጠይቁም እንዳልመጣ ተነግሯቸዋል፡፡

የታፈነው የመኢአድ አመራር ማዕከላዊ እንደሌለ የተነገራቸው ቤተሰቦቹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ከሆነ በሚል ሪጂስትራል ስሙ እንዳለ ቢያስጠይቁም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ከየ ክፍለ ሀገሩ በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታፍነው በአሁኑ ወቅት ማዕከላዊ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እና የመኢአድ አመራሮች በትናንትናው ዕለት አራድ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 21/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል

No comments: