Thursday, February 4, 2016

በጉጂ ዞን ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ቀንና ሌሊት እየተካሄደ ነው

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- ነጋዴው፣ የመንግስት ሰረተኞች፣ አርሰዶአሮችና የአካባቢው ህዝብ ቀንና ሌሎት ህዝባዊ እንቢተኝነቱን እየገፉበት መሆኑን ያነጋገርናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። 25 ዓመታት ዝርፊያ ሲያካሂድ የቆዬው የሼክ አላሙዲን የወርቅ ኩባንያ ከአካባቢው እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በደርሞ ወረዳ በኡዶ ሻኪሶ ኡኩቶ በሚባል አካባቢ ህዝቡ ጥያቄያችን ካልተመለሰ ከእንግዲህ ወደ ቤታችን አንገባም በማለት ተቃውሞ እያሰማ ነው።
ነዋሪዎች መብታችን ይከበር፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ ልጆቻችን እያለቁ እኛ የምንቀመጥነት ምክንያት የለም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን የሚናገሩት የአገር ሽማግሌ፣ ከወራት በፊት ሌሎች ያነሱዋቸው የመብት ጥያቄዎች ካልተመለሱ ሌትና ቀን የሚቆይ ተቃውሞ እንደሚያካሂዱ የስጡት ማሰጠነቀቄያ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን አክለዋል። ህዝቡ እሳት እያነደደ ሌትና ቀን ተቃውሞውን እየገለጸ መሆኑን፣ የፌደራል ፖሊሶች 100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ይዘው ማሰራቸውን ገልጸዋል


No comments: