Sunday, February 14, 2016

እስኪ በዚች ነገር ትንሽ እንመሰጥባት!

በዛሬ የአዲስ አበባ ገበያ አንድ ኩንታል ጤፍ 2200 ብር ነው። ይህ ማለት 1ኪሎው 22 ብር ማለት ነው። አንድ ኪሎ ጤፍ ደግሞ (መብራት፣ ትራንስፖርት፣ ጉልበትና ሌሎች የወጥ ወጪዎችን ሳይጨምር) አምስት እንጀራ ይወጣዋል። አምስት እንጀራ ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ ጠግቤ ልብላ ለሚል ሰው የአንድ ቀን ምግብ ነው።
...እስኪ በዚች ነገር ትንሽ እንመሰጥባት!
1) አድገናል ብለው ጆሮዋችንን የሚያደነቁሩትን ባለስልጣኖችን እንተዋቸውና ለመሆኑ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ደሞዛችሁ ስንት ነው? ስንት እንጀራ ነው በቀን የምትበሉት? አንድ የእድሜውን አጋማሽ ተምሮ ዲግሪ የያዘ ወጣት የወር ደሞዙ 1600 ብር ነው። ይህ ሰው አድጓል? በልቶ ነወ ጧት ወደ ስራው የሚሄደው?
2) ምናለ ሰው ሳልበላ አደርኩ፣ ኑሮ ተወዷል ብሎ እንዲናገር ቢፈቀድለት? ከረሀቡ ይልቅ ረሀቡን እንዳይገልጽ መደረጉ ይበልጥ ያገረጣል!
3) ነገ ለቫለንታይን አበባና ወይን፣ ቀይ ልብስና ኬክ፣ ሆቴልና ሬስቶራንት የምትራወጡ ወገኖች ሆይ እናንተ እድለኞች ናችሁ። መልካም በአል ይሁንላችሁ። ቢያንስ ግን በወር አንዲት ሺህ ብር ብቻ እየተከፈላቸው ኬሚካል እያሸተቱ በአበባ እርሻዎች ውስጥ የሚሰሩ ወገኖቻችሁን አመስግኑ።
4) እንዲህም እንድያም እያደረገ በዚህ ሁሉ መሀል በሰላም በጤና የሚጠብቀን ፈጣሪ ይመስገን!
(
የትነበርክ ታደለ)

No comments: