Tuesday, February 23, 2016

ኢትዮጵያ እንደ ሶሪያ ልትሆን እንደምትችል ሪፖርተርር አስጠነቀቀ

ብዙዎች አገራችን ኢትዮጵያ ወደ ገደል ዉስጥ እየገባች እንደሆነና ነገሮች በቶሎ ሰላማዊ መፍትሄ ካልተሰጣቸው የሲሪያ እድል እንደሚያጋጥማት ሲያስጠነቅቁ ነበር። የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ በብዙዎች የሚሰጡ ምክሮችን እና ማስጠንቀቂያዎችን በማጣጣል “ምን ታሟርታልአችሁ፤ እናንተ ተቃዋሚዎች እንጂ ሕዝቡ በኢሕአዴግ የልማት ጉዞ ደስተኛ ነው” ሲሉም ነበር።
የቀድሞ ሕውሃቱ አማረ አረጋዊ በባለቤትነት የሚመራው አገር ዉስጥ የሚታተመው ሪፖርተርር ጋዜጣ ግን በርእስ ንቀጹ ብዙዎቻችን ሲናገሩት የነበረዉን በማስፈር ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በገሃድ አፍጠርጥሮታል።
በባለስልጣናት መካከል መፈራራትን gridlock እንዳለ ይታወቃል። ማን ወሳኝ እንደሆነ፣ ማን መሪ እንደሆነ የማይታወቅበት አገር ሆናለች ኢትዮጵያ።
“የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ በመካከለኛ ደረጃ ያሉ አመራሮችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት እርስ በርስ እየተፈራሩ የሚሸፋፍኑ ከሆነ አገሪቱን የማትወጣበት አዘቅት ውስጥ ነው የሚከቷት” ያለው ሪፖርተር ኢሕአዴግ በአሰራር ደረጃ ትንሿንም ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ችግር እንዳለበት ለማሳየት ሞክሯል። በመልካም አስተዳደር, በሕግ የበላየነት ረገድ፣ መወሰንና ችግር አለብን ማለት ሳይሆን፣ በተግባር መስረታዊ የሆነ ለዉጥ ካለምጣ፣ አገሪቷ ወደ ከፋ ደረጃ እንደምትወድ ነው የገለጸው።
“ ባለንበት ዘመን በዓለም ዙሪያ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ በሶሪያ በየቀኑ በርካታ ሰዎች ይገደላሉ፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሶሪያውያን አልቀዋል፡፡ በመላው ዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተሰደዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከ400 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በጦር ቀጣናዎች ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ታግተዋል” ሲል በሶሪያ ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ የጠቀሰው ሪፖርተር፣ ሶሪያ ወደ ቀዉስ የገባችሁ ለዓመታት ሲንከባለሉ የነበሩ ችግሮች መፍትሔ ባለማግኘታቸው ዘግይቶ በተቀሰቀሰ አመፅ እንደሆነ ያስረዳል።
“አመፁ አቅጣጫውን ስቶ ሶሪያውያን ለእልቂትና ለመበተን ሲዳረጉ አገራቸው ደግሞ ወድማለች፡፡ ሕግና ሥርዓት ሲጠፋ ውጤቱ ቀውስ እንደሚሆን ያሰፈረው ሪፖርተር፣ “ አሁንም በአገራችን የሚታዩ የዘመናት ችግሮች እንዲፈቱ ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ችግሮችን እያድበሰበሱና ጊዜያዊ የማስታገሻ መፍትሔዎች ላይ ብቻ እያነጣጠሩ ፋታ ለማግኘት መሞከር፣ በሐሰተኛ ሪፖርቶችና መረጃዎች ላይ ብቻ በመንተራስ ችግሮችን ማንኳሰስና በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ግምገማ አለማድረግ ፈተናው የከበደ ነው። ነገር ግን አሁን ያሉትን ችግሮች አንጥሮ አውጥቶ በግልጽና በኃላፊነት መንፈስ መፍትሔ መፈለግ ለአገር ህልውና ጠቃሚ ነው፡፡ የዜጎች ግንባር ቀደም ተሳትፎ ሲታከልበት ደግሞ ውጤቱ አመርቂ ነው፡፡ በዚህ መሠረት መጓዝ ሲቻል ለጊዜው ከባድ የሚመስሉ ችግሮች በሙሉ ይፈታሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ አገር አንድ ላይ መቆም የግድ ይላል፡፡]ሁሉም ወገን ኃላፊነቱን ከተወጣ የማይፈታ ችግር የለም” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
ሪፖርተር ኢትዮጵያ እንደነ ሶሪያ ልትሆን እንደምትችል ቢጠቁምም፣ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግን በመጠኑም ቢሆን እንደ ሶሪያ፣ አገዛዙን የሚቃወሙ ነጻ መሬቶችንን እየተቆጣጠሩ፣ መንገዶች እየተዘጉ፣ የመንግስት ወታደሮችን ተቃዉሞዎችን መቆጣጠር እያቃታቸው እያለበት ሁኔታ እንደሆነ እየታየ ነው።
Source: Satenaw

No comments: