Thursday, February 4, 2016

ከወልቃይት ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ታሰሩ።


ESAT

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች ባደረሱን መረጃ መሰረት አዛዡ ኮማንደር ውለታው ትናንት ምሽት ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የፖሊስ አዛዡ ድንገት እስር የተዳረጉት የጎንደር ተወላጅ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ "የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ደጋፊናቸው" ተብለው ነው።
የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አገዛዙ ፈተና ከሆነበት ወዲህ እንደ ኮማንደር ውለታው ያሉ የጎንደር ተወላጆች ጥርጣሬ ውስጥ በመውደቃቸው በየሚሰሩባቸው መስሪያ ቤቶች ክትትል ሲደረግባቸው እንደቆየ ምንጮቹ ጠቁመዋል። ኮማንደሩ ትናንት ከመታሰራቸው በፊት - ታፍነው የነበሩትን 20 የኮሚቴው አባላትን ከማዕከላዊ እንደተለቀቁ በስልክ ደውለው እንዳገኛቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ወልቃይቶች፦"ላለፉት 25 ዓምታት ያለፍላጎታችን በግዳጅ በትግራይ ክልል ተካልለን ኖረናል፤ እኛ ግን አማራዎች ነን፤ ምንነታችን ላይ የሚደረግ ጫናን አንቀበልም" በማለት ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ ረዥም ጊዜያት ተቆጠረዋል።


No comments: