Monday, February 22, 2016

በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አድማሱን በማስፋት ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ ነው

ኢሳት (የካቲት 22 2008)
ሰሞኑን በምሽራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በሳምንቱ መገባደጃ ወደ በርካታ አካባቢዎች በመዛመት ላይ መሆኑ ተገልጿል። 
በስፍራው በመካሄድ ላይ ያለን ግድያና እስራት ለማውገዝ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ እሁድና ሰኞ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በአግባቡ ሊታወቅ ያልቻለ ሰው መገደሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። 
ይኸው ተቃውሞ ሰኞ በአዲስ መልክ በምስራቅ ወለጋ አካባቢም ሲካሄድ የዋለ ሲሆን በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውንና ድብደባ እንደተፈጸመባቸውም ታውቋል። 
የክልሉና የፌዴራል ባለስልጣናት ተቃውሞው በቁጥጥር ስር ዉሏል ቢሉም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ተቃውሞው በመቀጠል ላይ መሆኑን ገልጸዋል። 
በሃገሪቱ የሚዲያ አፈና በመኖሩ ምክንያት በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎችን ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለም እነዚሁ ድርጅቶች አስታውቀዋል። 
ሶስተኛ ወሩን የያዘው ይኸው ተቃውሞ ሰኞ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ማገርሸቱንም ከሃገር ቤት ከተገኙ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

No comments: