Wednesday, February 10, 2016

ኢንቨስተሮች በውጭ ምንዛሬ እጥረት መማረራቸውን እየገለጹ ነው

የካቲት (ሁለት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በአገሪቱ ውስጥ የሚታዬው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አስመጪና ላኪ ነጋዴዎች የመተማመኛ ሰነዶችን ከፍተው የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አንድ አመት ያክል ጊዜ ለመጠበቅ እየተገደዱ ነው። ችግሩ ከዛሬ ነገ ይፈታል ብለው የጠበቁ ነጋዴዎች አማራጭ በማጣት ፊታቸውን ወደ ጥቁር ገበያ አዙረዋል። ይህም ከባንኮች ውጭ በአገሪቱ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ የሚሸጡ ድብቅ ሱቆች እንዲስፋፉ አድርጓል።
ነጋዴዎች ምሬታቸውን በተደጋጋሚ እየገለጹ ቢሆንም፣ እስካሁን ችግራቸውን የሚሰማላቸው አካል ማጣታቸውን ይናገራሉ። መንግስት ለሚያስገነባቸው ግንባታዎች ቅድሚያ በመስጠቱ የግል አስመጪ ነጋዴዎች የምንዛሬ እጥረቱ ተጎጂዎች ሆነዋል። የአገሪቱ የውጭ ንግድ መቀዛቀዙም ችግሩን አባብሶታል

No comments: