Tuesday, April 26, 2016

ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን?

ግን ሀገር ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ።ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉጎጠኝነትአንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊትዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?

በመጀመሪያራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውንርስ-ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣ ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች።
ያሳዝናልተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….
ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስተም
በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……

No comments: