Wednesday, April 27, 2016

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲሱ ትውልድ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲጠብቅና የታሪክ ህፀፆችን እንዲያርም ጥሪ አቀረበ



የኢትዮጵያ አንድነት የመጠበቅና የታሪክ ህፀፆችን ማረም ከአዲሱ ዘመንት ዲሞራቶች ይጠበቃል ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ። ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋየዘንድሮ ግንቦት 20” በሚል ርዕስ ሰሞኑን ከወህኒ ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ፅሁፍ ኢህአዴግ ወደስልጣን የመጣበትን 25 አመት በማስመልከት ያለፉትን 50 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።
በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ የነበረው የሃይል አሰላለፍ እንዲሁም በህብረ-ብሄርና በብሄር ፓርቲዎች መካክል የነበረውን ልዩነት በመዘርዘር ለኢትዮጵያ ችግር ዘላቂ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ አቅርቧል።
ተማሪዎች እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ 55 ዓመታት በኋላም የዮሃንስና የምኒሊክ 19ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ የፈጠረው ሽኩቻ የኢህአዴግ ቅኝት ጸረ-ዲሞክራሲ እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት ግብዓቶች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሲያጠቃልልምየታሪክ ጣጣ የኦሮሞና የሶማሌ ብሄርተኞችን ነፍስ ዕረፍት እየነሳ ነው፥ የታሪክ ህፀጾች የማይቀበሉ ቀላል የማይባሉ የፖለቲካ ሃይሎችም አሉ፥ ይህ ሁሉ ተደማምሮ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው፣ መፍትሄውም ከአዲሱ ዘመን ዲሞክራቶች ይጠበቃልበማለት ለሃገሪቱ ችግር ዕውነተኛና ዘላቂ መፍትሄ እንደሚጠበቅ ጥሪ አቅርቧል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመስከረም ወር 2004 ጀምሮ በአሸባሪነት ተከሶ በወህኒ ቤት የሚገኝ ሲሆን፣ 18 ዓመታት እስር እንደተፈረደበት ይታወቃል። ክሱም ሆነ ፍርዱ እውነትም ሆነ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ለማመልከት ወይንም በፖለቲካ አመለካከቱ መታሰሩን ለማስረዳት በጽሁፉ ግርጌየህሊና እስረኞችሲል አስፍሯል።

Esat News


No comments: