Saturday, November 9, 2013

በዛሬው የኢህአዴግ ስብሰባ ሀይለማርያም ደሳለኝ አንድ ታላቅ ዜና ለማብስር ተዘጋጅተው ነበር

በዛሬው የኢህአዴግ ስብሰባ ሀይለማርያም ደሳለኝ አንድ ታላቅ ዜና ለማብስር 

ተዘጋጅተው ነበር፣ የህወሀት የጸጥታ አማካሪዎቻቸውን "ድንቅ" ችሎታ ለማወደስ 

ቃላትን ከሽነው ሲያጠኑ ሰንብተዋል፤ ባለፈው ሰሞን ስለግንቦት 7 ተጠይቀው " 

ህልመኞች ናቸው የትም አይደርሱም" ያሉት ይህን " ወያኔ ኦ ሚሊኒየም" 

የተባለውን ፕሮጀክት ተማምነው ነው። 

ሀይለማርያምና የህወሀት የጸጥታ አማካሪዎቻቸው ህልማቸው ተኖ ሲቀር 

አንገታቸውን ደፍተው ስብሰባቸውን እያካሄዱ ነው። 


ህወሀት የፖለቲካ ሰዎችን በመግደል ረጅም ርቀት የሚጓዝ አይመስለኝም፤ የነጻነት 

ትግል የነጻነት መሪውን በመግደል እንደማይቆም ታሪክ ይናገራል፤ አንዳርጋቸው 

ቢሞት ሺ አንዳርጌዎች መፈጠራቸው አይቀርም። ይልቅ ይህ አካሄድ የሚጎዳው 

ህወሀትን ነው። የህወሀት መሪዎች የት እንደሚጠጡ፣ የት ሰክረው እንደሚወድቁ፣ 

የት እንደሚመገቡና የት እንደሚውሉ ይታወቃል። ግንቦት 7 ትግሉ በዚህ መንገድ 

ይካሄድ ብሎ ከወሰነ፣ ህወሀት ከሚያደርሰው ጉዳት የበለጠ ሊያደርስ ይችላል። እኔ 

እስከማውቀው፣ ግንቦት7 እስከዛሬ በህወሀት መሪዎች ላይ እርምጃ ሊወስድ 

ያልፈለገው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አገሪቱን የሚመራ ሀይል ባልተደራጀበት ሁኔታ 

እንዲህ አይነት እርምጃ መውሰዱ በአገር ላይ ጉዳት ይደርሳል ብሎ ስላሰበ ነው። ያ 

ባይሆን ኖሮ መለስ ቤልጂየም ለህክምና በሚመላለስበት ወቅት ብዙ ጉዳት 

ሊያደርስበት ይችል ነበር፣ ግንባሩ የጠባቂዎችን የጠመንጃ ቁጥር ሳይቀር ይፋ 

ማድረጉን አንረሳውም። ግንቦት7 ለዚህ ድርጊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል? በጊዜ 

የምናየው ይሆናል።

No comments: