Saturday, November 9, 2013

Assassination Plot Against Ginbot 7 Forces Leaders Foiled: ESAT Reports

Assassination Plot Against Ginbot 7 Forces Leaders Foiled: ESAT Reports

Nov. 09, 2013
ESAT has reported that an assassination plot to kill Andargachew Tsige, the Secretary General of Ginbot 7 Movement and the leaders of Ginbot 7 Popular Force (G7PF) has been foiled. The operation was masterminded by Getachew Assefa, Head of Ethiopia’s National Intelligence and Security Service (NISS) and Tsegaye Berhe, the Prime Minister’s Security Adviser.
ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ።
ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል።
ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም በሚል የተመራው የግድያ ዘመቻ -በነገው እለት ጥቅምት 30/2006 ዓ/ም ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበር የድምጽ መረጃው ያመለክታል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ሰራዊት የምረቃ በአል በነገው እለት የሚካሄድ መሆኑን መነሻ በማድረግ በእለቱ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎችንና የኤርትራ ባለስልጣናትን ለመግደል የታቀደው ዘመቻ ከመነሻው ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ፣ በፍጻሜው ዋዜማ ላይ ሲደርስ ሙሉቀን መስፍን የተባለውን ለግድያ የተላከውን ግለሰብ ህዝባዊ ሀይሉ በቁጥጥር ስር በማድረግ ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም የተባለው ኦፕሬሽን ከሽፏል።

No comments: