Thursday, November 28, 2013

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።

«ሰው ለሰው» የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ።
ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል።
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል። ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።Image

No comments: