Thursday, April 17, 2014

የህወሓቶች የይቅርታ ሂደት የሚሳካ አይመስልም!


የህወሓቶች የይቅርታ ሂደት የሚሳካ አይመስልም!
አብርሃ ደስታ
ህወሓቶች ህዝብን "ይቅርታ" የመጠየቅ ሂደቱ የሚሳካላቸው አይመስልም። ምክንያቱም ህዝብ መሰብሰብ አልቻሉም። ህዝብ ለህወሓት ስብሰባ ሲጠራ አይገኝም። ለምሳሌ የዓዲግራት ህዝብ በህወሓት ስብሰባ ለመገኘት ፍቃደኛ አልሆነም። እናም ህወሓቶች ህዝብ ለመሰብሰብና ይቅርታ ለመጠየቅ መጥተው የራሳቸው ካድሬዎች እየሰበሰቡ ዳጎስ ያለ የዉሎ አበል እየከፈሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ እያፅናኑ "በደም የተገኘ ስልጣን እንደ ቀልድ በቀላሉ" ለሌሎች እንደማይሰጥ ለህዝብ መናገር እንዳለባቸው ይነግሯቸዋል። ከህዝብ ጋ ለመገናኘት የመጡ የህወሓት መሪዎች አሁን አሁን ደግሞ የእርሻ ወይ የመስኖ ልማት ለማየት ነው የመጣነው እያሉ የህዝብን ጥያቄዎች ላለመመለስ እያንገራገሩ ነው። በብዙ የትግራይ አከባቢዎች ህዝብ ባለመሰብሰብ ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን የዓድዋ ህዝብ (የፈረስማይ ሓሓይለ) ግን ጥያቄ አለን፣ አነጋግሩን ብሎ ሲጠይቅ በህዝቡ ስሜት የተደናገጡ የህወሓት መሪዎች ወደነበሩበት ተመልሰዋል። አሁን ሂደቱ ስላልተሳካ በሚቀጥለው ወር ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተደርጎ ህዝቡ ለማባበል አስተዳዳሪዎች "Self Criticism" ያደርጋሉ። በዚሁ ሂደት ብዙ የህወሓት አባላት "ዓረና" እየተባሉ ይባረራሉ። በህወሓት ዉስጥ ያሉ የዓረና ደጋፊዎች ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ እመክራለሁ። ማንም የህወሓት ሰው "ዓረና ነኝ" ማለት የለበትም።
It is so!!!

No comments: