Tuesday, April 1, 2014

ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ

ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ

ኢቲቪ ተመጣጣኝ የማስተባበያ አየር ሰዓት ለአንድነት ፓርቲ እንዲሰጥ ታዟል
download (1)download

የዘገየ ፍትህ እንደተሰጠ ባይቀጠርም በአንድነት ፓርቲ እና በኢትጵያ ቴሌቪዥን መካከል “አኬልዳማ ዘጋቢ ፊልምን አስመልክቶ ለነበረው 3 አመታትን ለፈጀ ክርክር ለአንድነት ፓርቲ ፈርዶ መቋጫ ሰጥቶታል በመሆኑም ኢ.ቲ.ቪ የአንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ ተመጣጣኝ የማስተባቤ አየር ሰዓት ለአንድነት እንዲሰጥ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ችሎቱን የተከታተለው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተ ነፃነት “ውሳኔ
የአንድነት ፓርቲ ክስ ኢ.ቲቪ የሰራው አኬልዳማ ዶክመንተሪ የፓርቲውን መልካም ስም እና ክብር ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገወጥ ድርጊት ነው የሚል ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም በአንድነት ላይ በደል ተፈፅሟል ሲል ኢቲቪ ጥፋተኛ ነው ያስተባብል ሲል ወስኖበታል፡፡” በማለት አስረድቷል፡፡

Source: http://www.fnotenetsanet.com

No comments: