Monday, July 14, 2014

የመአከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ነገ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ


የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑትን ወጣት ሀብታሙ አያሌውንና አቶ ዳንኤል ሺበሺን ለሰባት ቀናት አስሮ እስከ አሁን ፍርድ ቤት ያላቀረበው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ እና የመአከላዊ ወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኮማንደር ተክላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዘው የታሳሪዎቹ ጠበቆች ባቀረቡት ክስ መሰረት ነው፡፡
ዛሬ ሀምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ፍ/ብሔር ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የመአከላዊ ወንጀል ምርመራ ሀላፊ ኮማንደር ተክላይ ታሳሪዎቹን ይዘው በነገው ዕለት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተወስኗል፡፡

No comments: