Tuesday, July 15, 2014

ፖሊስ እነ ሐብታሙ አያሌውን ፍ/ቤት አቅርቤያለሁ አለ


ፓርቲውና የታሳሪ ጠበቆች መቼ፣ እንዴትና የት እንደቀረቡ ምንም መረጃ እንሌለ አረጋግጠዋል


ዛሬ ሀምሌ 7 ቀን 2006 . የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ /ብሔር ችሎት ሀምሌ 6 ቀን 2006 . በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራቱ ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡ 
ችሎቱ 330 ተሰይሞ ተከሳሽ ክሱ እንደደረሳቸው ዳኛው ጠየቁ፡፡ ክሱ በንባብ ከተሰማ በኋላ የጽሑፍ ምላሽ እንዳላቸው ሲጠየቁ፣ በጽሑፍ መልስ አላመጣሁም በቃል መልስ እሰጣለሁ በማለት ምላሻቸውን ከዚህ እንደሚከተለው በቃል ሰጥተዋል፡፡
ተከሳሾቹ በሰኔ 30 ቀን 2006 . በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ ሐምሌ 1 ቀን 2006 . እንደተያዙና ሐምሌ 2 ቀን 2006 . /ቤት ቀርበው ቀጠሮ እንደጠየቁባቸውና በህጉ መሰረት መብታቸው ተጠብቆ እንዳለ ገልጸው ጠበቆቹ ከደንበኞቻቸው ጋር ረቡዕ እና ዓርብ መገናኘት እንደሚችሉ የመጡበት ቀን ግን መገናኘት በማይቻልበት ቀን በመሆኑ ነው ያልተገኙት በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡
የከሳሽ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ ይርዳው በበኩላቸው ይህ በቃል የተሰጠው ምላሽ በሰነድ ያልተደገፈ ማስረጃ የሌለው በመሆኑ የተከበረው /ቤት ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡ ወደ ማዕከላዊ በመሄድ ደንበኞቻችንን ለማናገር እስረኞች አስተዳደር ብናናግርም የፀረ ሽብር ኃላፊውን አናግሩ የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን ኃላፊውን ማናገር አልቻልንም በቀጠሮ መጥተን እናናግራቸው ብንልም በቀጠሮ ሊያገናኙን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የኛ ጠበቃ ጓደኞች ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ አይተናል እኛ ደንበኞቻችንን እንዳናናግር ተደርገናል፣ አድልዎ ተደርጎብናል፡፡ ምንም እንኳ ሀገሪቷ በወታደራዊ ዕዝ ሥር ብትሆን እንኳ የእስረኞች የእኩልነት መብት አይገፈፍም፡፡ ሌላው የፀረ ሽብር ኃላፊው እንዳመኑት በሳምንት ሁለት ቀን ረቡዕና ዓርብ ብቻ ከእስረኞች ጋር መገናኘት ይችላሉ ያሉት የህግ ጥሰት ነው፣ ለምን በሥራ ቀናቶች ሁሉ መጠየቅ አለባቸው ይህ ህገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ታሳሪዎቹን ፖሊስ ይዞ እንዲቀርብ ያዘዘ ቢሆንም የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ ታሳሪዎቹን አላቀረበም፡፡ በአቤቱታችን መሰረት ደንበኞቻችን ህጉ ተጠብቆ በህጉ መሰረት ያልተያዙ በመሆኑ አሁኑኑ ከእስር እንዲለቀቁልን፤ ይህ የማይሆን ከሆነ በዋስትና እንዲለቀቁልን ክቡር /ቤቱን እንጠይቃለን፡፡ የእስር ቦታቸው ተቀይሮ ወደ ተሻለ ጣቢያ ተዛውረው በጠበቃ፣ በወዳጅ ዘመዶቻቻ እንዲጎበኙ እንዲደረግ ክቡር /ቤት እንጠይቃለን፡፡ በማለት የከሳሽ ጠበቆች ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም /ቤቱ የመያዣ ትዕዛዝና /ቤት ያቀረቡበትን ሰነድ የማዕከላዊ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ተክላይ መብራህቱ ሐምሌ 10 ቀን 2006 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይዘው እንዲቀርቡ አዟል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከሥራ ሰዓት ውጪ ማታና ጠዋት ታሳሪዎችን እንደሚያቀርቡ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

No comments: