Wednesday, March 19, 2014

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማነው???(አብርሃ ደስታ)

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማነው???(አብርሃ ደስታ)


መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከትእምት ኩባንያዎች አንድ ሲሆን በመቀለ ከተማ ይገኛል። አንድ በጣም የወረደ ግን አስገራሚ ነገር ልንገራቹ። በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚሰሩ ሰራተኞች በሙሉ የአንድ ሐረግ ቤተሰብ አባላት ናቸው። ግን የአንድ ትልቅ ፋብሪካ ሰራተኞች እንዴት የአንድ ቤተሰብ ሊሆኑ ይችላሉ? ለኔም ገርሞኛል። ግን "ብታምኑም ባታምኑም" የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በሙሉ በዘመድ አዝማድ የተሰባሰቡ ናቸው። ከሌላ የትግራይ አከባቢ የመጣ ሰው የፈለገ ብቁ ቢሆን፣ የፈለገ የትምህርት ደረጃ ቢኖረም የነሱ የቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር አይቀጠርም። ዘመድ ከሆነ ግን ትምህርት ቢኖረውም ባይኖረውም ይቀጠራል።

በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባሰ እንጂ በብዙ መስራቤቶችና ድርጅቶች ተመሳሳይ ነው። ሰዎች የሚቀጠሩ በብቃታቸውና በሙያቸው ሳይሆን በፖለቲካ ታማኝነታቸው ነው። የፖለቲካ ታማኝነታቸው የሚረጋገጠው ደግሞ የመጡበትን (የተወለዱበትና ያደጉበት) አከባቢ ግምት ዉስጥ በማስገባት ነው። ያደጉበት አከባቢም በራሱ በቂ አይደለም። የባለስልጣናቱ የቅርብ ዘመዶች መሆን አለባቸው። አዎ! ስራ ለማግኘት የባለስልጣናቱ የቅርብ ዘመድ መሆን አለብህ። ይሄ እውነት ነው። ማመን ያልፈለገ ካለ ሁኔታው ያጥናና እቅጩ ይወቅ።

በሀገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆንን። በሀገራችን ስራ ለማግኘት የግድ የባለስልጣናት ዘመድ መሆን ያለብን አይመስለኝም። ይቺ ሀገር የሁላችን ናት። ለሁላችን መሆን አለባት። 

It is so!!!


No comments: