Tuesday, November 8, 2016

የሠማያዊ ፓርቲ ሠማኒያ አባላት እስር ላይ ናቸው

ሠማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች አንዳንድ የአመራር አባላትን ጨምሮ ከሠማኒያ በላይ አባሎቹና ደጋፊዎቹ መታሰራቸውን አስታወቀ፡፡
ከእነዚህም መካከል ፍርድ ቤት የቀረቡት ሦስት ብቻ መሆናቸውን የገለፁ አንድ የፓርቲው አምራር አባል ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዛዝን ባለመቀበል በዋስ የተፈቱ አንዲት አመራር አባል በእስር እንደሚገኙ ተናግረዋል፤ የፖሊስን ምላሽ ለማግኘት አልተቻለም፡፡
የሠማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሠለሞን ተሰማ ለቪኦኤ እንደገለፁት በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እጅግ ብዙ የሠማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እስር ቤት ይገኛሉ፡፡
የህዝብ ግንኙነቱ ኃላፊው  በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በየካ ክፍለ ከተማ በቤላ ፖሊስ ጣቢያ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ላዛሪት ፖሊስ ጣቢያ፣ በአራዳ ክፍለከተማ ገዳም ሰፈር ፖሊስ ጣቢያ እንዲሁም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኳስ ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ 85 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችና ደጋፊዎች መታሰራቸውን ገልጸዋል። ከነዚህም ውስጥ የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ አበበ አካሉና የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ብሌን መስፍን እንዲሁም የፓርቲው  የምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው ከበደ ይገኙበታል።

VOA

No comments: