Thursday, November 12, 2015

የሁለት ቀን የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ

በኢትዮጵያ በተከሰተው ርሃብ ላይ በእንግሊዘኛ ‪#‎EthiopiaFamine እንዲሁም በአማርኛ ‪#‎ክፉ_ቀንበሚል መለያ (ሀሽ ታግ) የሁለት ቀን ዘመቻ ይደረጋል፡፡ ዘመቻው አርብ ህዳር 3/2008 . እና ቅዳሜ ህዳር 4/2008 . ለሁለት ቀን የሚደረግ ሲሆን በመጀመሪያው ቀን ስለ ርሃቡ መረጃዎች በመለዋወጥ፣ ለኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ርሃቡን በማሳወቅ ላይ ያተኩራል፡፡
የሁለተኛው ቀን ዘመቻ መፍትሄዎችን በማፈላለግ በተለይም በርሃቡ የተጠቁትን በምን መልኩ መርዳት እንዳለብን በመወያየት ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡
#EthiopiaFamine
#
ክፉ_ቀን

No comments: