Thursday, February 6, 2014

አቶ አስራት ጣሴ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ

አቶ አስራት ጣሴ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዙ

የአንድነት ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘዘለፋ አዘል ጽሑፍጽፈዋል በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ተላለፈባቸው፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዘጠነኛ ፍትሐብሔር ሁለተኛ የቤተሰብ ችሎት ጥር 21 ቀን 2006 .. ወጪ ያደረገው የትዕዛዝ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ አቶ አስራት ጣሴ በአዲስ ጉዳይ ሳምንታዊ መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 198 የጥር ወር 2006 .. ዕትም አንድ መጣጥፍ አቅርበዋል፡፡ ‹‹… አሁን ግሞ ከሰሞኑአኬልዳማድራማ በድጋሚ በተከታታይ እየቀረበና እየታየ ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን በስም ማጥፋት ወንጀል በፍርድ ቤት ከሶ ገና ውጤት ባልተገኘበት ወቅት ነው፡፡ እሱም ፍትሕ ከኢሕአዴግ ፍርድ ቤቶች ይገኛል ተብሎ ሳይሆን፣ በታሪክ ምስክርነት እንዲመዘገብ ሲባል ነው፤›› የሚል ጽሑፍ ማቅረባቸውን ፍርድ ቤቱ በፖሊስ በኩል ለአቶ አስራት እንዲደርሳቸው ባስተላለፈው የትዕዛዝ ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከላይ በትዕዛዝ ደብዳቤው ላይ ያሰፈረውንና አቶ አስራት በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ጽፈውታል የተባለውን ጽሑፍ ‹‹ፍርድ ቤት ፍትሕ የማይሰጥ አካል መሆኑን የሚገልጽ ዘለፋ አዘል ጽሑፍ›› ሲል ገልጾታል፡፡

በመሆኑም መዝገቡ ከመመርመሩና ማለትም አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከሳሽ ሆኖ የቀረበበትንና የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትና የድርጅቱ ሠራተኛ የሆነው ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ተከሳሾች የሆኑበት መዝገብ ከመመርመሩ በፊት፣ የአቶ አስራትን ጉዳይ ማጣራት አስፈላጊ ሆኖ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም አቶ አስራት ጣሴ ጥር 30 ቀን 2006 .. ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ደብዳቤው እንዲደርሳቸው ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በክስ ሂደትላይ ያለውን የአኬልዳማ ዶርመንተሪ ፊልም በቅርቡ በድጋሚ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

No comments: