Wednesday, February 26, 2014

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂ ምላሽ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂ ምላሽ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አንድነት ፓርቲ ለላከለት ማስጠንቀቂ ምላሽ መስጠቱን የአንድነት ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት በቅርቡ አንድነትን በ“አሸባሪነት” የሚፈርጅ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ ድርጅቱ ምላሽ እንዲሰጥ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለደብዳቤው ምላሽ ባለመስጠቱም አንድነት በድጋሚ የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በጻፈው ደብዳቤ በ15 ቀን ውስጥ ምላሽ ካላገኘ ወደ ክስ እንደሚሄድ አስጠንቅቆ ነበር፡፡
ማስጠንቀቂያው የደረሰው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ለአንድነት ማስጠንቀቂያ ሁለት ገፅ ያለው ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምላሽ ላይ ከተወያየ በኋላ ምላሹ ትክክለኛ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ጉዳዩን ለፓርቲው የህግ ክፍል እንዲመራ መወሰኑን የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ዘጋቢ ፊልም አንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ በፓርቲው መከሰሱ አይዘነጋም፡፡

No comments: