Thursday, December 10, 2015

ጊዜው ያስፈራል!! (በስንታየሁ ቸኮል)

ለሁሉም ነገር ጦር ሳይሆን ነጻነት ችግሩን ይቀርፋል፡፡ ሁሉ ነገር ያስፈራል ህዝብ በቃኝ ካለ አልበቃህም እንዴት ይባላል?
በየትኛውም መመዘኛ ሰው ከተገፋ በደል ጭቆና ከበዛበት የመከራው ስቃይ ከሚችለው በላይ ከሆነ በሚወስደው ሰቅጣጭ እርምጃ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችል የሞራልም የህግም ተቀባይነት የለውም፡፡
አማራጭ በሌለን አንድ ደሀ ሀገር በሀሳብ ተስማምተን አብሮ ለመኖር እንዳንችል መለስ ቀብሮት ያለፈው ፈንጅ አደጋው እየመጣ ነው፡፡ የትግሬ ነብስ በመለስ አስተሳሰብ ወርቅ አድርጎት የኦሮሞው የአማራው ሌሎችም ወገኖች ነፍስ ቀይ ደም እንደሌለው ተቆጥሮ የዚህ ውላጅ ራዕይ ተሸካሚዎች የሰው ደም እየፈሰሰ በዝምታ እያረጋገጡት መሆኑ ወዴት እየሄድን ነው? አደገኛ ደም መፋሰስ በዚች ምስኪን ሀገር እያንዣበበ መሆኑ ይሄ ጠቋሚ ነው፡፡ ጊዜው ያስፈራል፡፡
97 ደፍተሩን ይዞ ጥይት እንደተሰጠው ህጻን ነብዩ ዛሬም ወረቀት በያዙ ተማሪዎች ሰው እያለቀ ጥቂት ዘረኛ ተከታይ ደጋፊዎች ገዳዮችን እያዩ ዝም ማለት የመጨረሻው መጠፋፊያ በየ በራችን ላይ ደርሷል፡፡
ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ እንደ ሰው የሁሉም ደም ቀይ ነው፡፡ ጥቂት ትግሬዎች ገዢ ሌላው ከነሱን ገበታ ትሪ የሚጠርግ አድርጎ ከዚህ በኃላ ማሰብ ለመጠፋፋት ካልሆነ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
ዛሬ አገሪቷን ለማዳን አርቆ አሳቢ ሰው ትሻለች በየአካባቢው የምንሰማው የህዝብ ብሶት ቤት ለቤት ቆንጨራና ገጀራ እየያዘ የሚወጣ ህዝብ እየመሰለ ያስፈራል፡፡ ቢሆንስ ማን ያውቃል?
እውነት ነው የምለው በጣም ያስፈራል፡፡
የትግራይ እናቶች ልጇ በጥይት ሲሞት አምረው እንደሚያለቅሱት ሁሉ የአማራው የኦሮሞው እናት የሚያለቅሱት እንባ በምን ይለያል? እነሱ ሰው አይደሉም? አገር ለማዳን እባካችሁ ቀኑ ሳይረፍድ አስቡ ለሁሉም የምትሆን አገር ዛሬ ፍጠሩ ሰው መግደል መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡
የበለጠ ችግሩን ከማስፋት ወጪ ህዝብ አምሮ ከተነሳ በአንድ ጀንበር ሊጎርሳችሁ ይችላል፡፡ አሁን የሚታየው እሱ ነው፡፡ ቅን ሁኑ በቃ ሀያ አምስት አመት የደም ዋጋ የምትሉት አሁን ያለቀ መሆኑን ካልተረዳችሁ ነገ ሁሉንም በማጣት እንዳትማሩ ያስፈራል፡፡ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ ለሁሉም ነገር መፍትሄ ጦር ሳይሆን ነጻነት ነው፡፡
ህዝብ ከተነሳ ድል የህዝብ ነው!!!!

Source: Millions of voices for freedom - UDJ


No comments: