ከፍተኛ የህወሃት ባለስልጣናት ሰሞኑን በዝግ ስብሰባ ተወጥረው ሰንብተዋል። ከታመኑ ውስጥ አዋቂዎች በደረሰን መረጃ መሰረት በኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ሙሉ ለሙሉ በሃይል ለመደቆስና አመጹ ወደ ሌሎች ክልሎች እንዳይዛመት የሃይል እርምጃ ለመውሰድና በጅምላ ያለርህራሄ ለማሰር ውሳኔ አስተላልፈዋል። የተፈጠረው ቀውስ በኦህዴድ ላይ የተሳበበ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታም ብአዴኖችም የማይታመኑ መሆናቸው ተወስቷል። ሁለቱ የህወሃት ተለጣፊ ድርጅት አመራሮችና ካድሬዎች እንዲበወዙ በሰራዊቱ ውስጥ ያሉ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በተለይ አፈሙዝ በስርአቱ ላይ ሊያዞሩ ስለሚችሉ ሃላፊነት እንዳይሰጣቸው እንዲሁም ትዛዝ አንቀበልም የሚል ስሜት ያላቸውን በሙሉ ማሰርና ማሰናበት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በሃይል አመጹን ለመደቆስ እቅድ የነደፉ ሲሆን የስልክና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ብርቱ ቁጥጥር ለማድረግ ከተቻለ ፌስቡክ፣ ዩቱብ፣ ቲዊተር የመሳሰሉን ኢትዮጵያ እንዳይደርሱ እንዲደረግ ታቅዷል። ከሁሉ የከፋው እቅድ አመጽ በተነሳባቸው ወይንም ሊነሱ በሚችሉባቸው አካባቢዎች የብሄረሰብ ግጭት፣ በተለይ በአማራና በኦሮሞ ብሄር መካከል፣ በስፋት ማስነሳት ወሳኝ መሆኑን ህወሃቶች አምነውበታል። ህወሃት በአሁኑ ግዜ የተጨነቀ እባብ ስለሆነ ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ በማድረግ ትግሉ የሁሉንም ኢትዮጵያዊን ብሶትና ጥያቄ ባካተተ መልኩ ከዳር እስከዳር ባንድነትና በመተባበር ስሜት ተጠናክሮ ይቀጥል።
No comments:
Post a Comment