Saturday, December 5, 2015

ወይኔዎች በአዳማ ተሰብስበዋል


ሕወሃት በኦሮሚያ ክልል የተነሱ ተቃዉሞዎችን ለመቆጣጠር በአዳማ ሚስጥራዊ ስብሰባ የጠራ ሲሆን የክልሉ የሕወሃት አገልጋይ ኦህደድ ሃላፊዎችም እንዲገኙ ተደርጓል። የስብሰባው ሚስጥር በኦዲዮ በሚስጠር እንዳይወጣ የኦሮሚያ ፕሬዘዳነት አቶ ሙክታር ከድርን ጨመሮ፣ እምነት ሰለምይጣልላቸው ስልካቸውም ዉጭ አስቀምጠው ወደ ስብሰባው የገቡት።
በተያያዘ ዜና፣ የሚነሱ ተቃዎሞዎችን ለመቀነስም፣ ህወሃት ማስተር ፕላኑን ለጊዜው ለማስተላለፍ እንደወሰነም ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
ማስተር ፕላኑ ለጊዜውተላለፈ ቢባልም፣ መሰረታዊ የስርዓት ለዉጥ ካልመጣ፣ ገበሬው የመሬት ባለቤት ካልሆነ፣ የሚለወጥ ነገር የለም። በመሆኑም ሕወሃቶች በሚያደርጉት የተለያየ ታክቲካል ማዘናጊያ ሳንወናበድ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የቆመና ሕዝብን በትክክል የሚያገለገል ስርዓት ለመዘርጋት ሁላችንም መንቀሳቀስ ይኖርብናል።

Source: ሚሊዮኖች ድምጽ

No comments: