Wednesday, December 2, 2015

"ሚራክል እድገት,,,,, ሚራክል አዋጅ,,,,, በሚራክሉ ኢቢሲ "


(አሌክስ አብርሃም)
ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ (እንባ ጠባቂ የሚባለው ተቋም ሃላፊ መሰሉኝ)ዛሬ ማታ በኢቢሲ በተላለፈና የመረጃ ነፃነት አዋጅ አፈፃፀም ላይ ለመምከር በተደረገ ስብሰባ ስለመረጃ ነፃነት አዋጁ ዘግይቶ ስራ ላይ መዋል ተጠይቀው ምላሽ ሲሰጡ ይህን በእጃቸው የያዙትን ቀይ መፅሐፍ እያሳዪ,,,,
" እዚህ ውስጥ ሚራክል ነው ያለው,,,, " አሉ!
እኔ ደግሞ ይሄ በጃቸው የያዙት መፅሃፍ ቅዱስ ይሆን ቁርዓን ብየ "ስንቄ ነይ መነፅሬን አቀብይኝ " አልኩና ሳየው,,,,, ሶስት አመት ከርሞ ስራ ላይ የዋለው እንደራሳቸው ክብርት ፎዚያ አባባል ( ገና በደንብ ሳያልቅ የተቀመጠውን ጊዜ ለማክበር ሲባል ስራ ላይ የዋለው) የመረጃ ነፃነት አዋጅ ነው:)
እኔማ "እንባ ጠባቂ ተቋም,,,, እንባ መጠበቁን ትቶ እንደብዙሃኑ ኢትዮጲያዊ ጌታን መጠበቅ የጀመረ መስሎኝ አሁን ዘየደ ብየ ነበር:),,,, እውነቴን እኮ ነው,,,, በዚህ ሰዓት ወደፈጣሪ እንጅ ወደእንባ ጠባቂ ተቋም እንባውን የሚረጭ ዜጋ እንብዛም ነው,,,,,
በነገራቸን ላይ ስለመረጃ ነፃነት "እንመካከር " ብለው ተሰብስበው እርስ በርስ ሲወነጃጀሉና አንዱ አንዱ ላይ ጣቱን ሲቀስር የአገራችን ተቋማት ይሄን የፈረደበት ህዝብ መምከር እንጅ እርስ በርስ መመካከር እንደማይሆንላቸው ፍንትው ብሎ ይታይ ነበር! !
,,,, መንግስት ያስቀመጣቸው ባለስልጣናት ናቸው መረጃ የማይሰጡት,,,,, የለም ጋዜጠኛው ነው ችግር ያለበት,,,, ንትርክ,,,,, ሳምሶን ማሞ "እንባ ጠባቂ እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አደረገው ይላል,,,,
ክቡር ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው እረዳ " ህዝቡ ስለአዋጁ ምንም ግንዛቤ የለውም እንጅ መስሪያ ቤታችን ያደረጃጀት ችግር የለበትም " ይላሉ,,,,(ማነው ግንዝባቤ መፍጠር ያለበት የሳቸው ቢሮ መስሎኝ ነበርኮ ) ኢቢሲን የወከሉ አንዲት ወይዘሮ ደግሞ ሳምፕል የተወሰዱ ተጠያቂወች ላይ "የሳንፕሉ መቶ ፐርሰንት" ተብሎ የተገለፀው ጉዳይ ትንሽ "ሮኬት ሳይንስ" ነገር ሁናባቸው ነው መሰል,,,, "ህዝቡ መቶ ፐርሰንት ስለአዋጁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል ትንሽ አልተጋነነም ?" ይላሉ,,,, እዛጋ የሆነ ሰውየ በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ማዛጋት ያዛጋል,,,,,አንድ ተናጋሪ ግን አሳዘኑኝ "ለጋዜጠኛ መረጃ መስጠትን ምፅዋት እንደመስጠት የሚቆጥሩት ተቋማት አሉ "
ሌላኛው "እና እንደአሁኑ ወሳኝ ስብሰባ ላይ ሁነን መረጃ ስጡን ስትሉንስ ለመረጃ ብለን ስብሰባ ረግጠን ልንወጣ ነው? ,,,, ከበሮ በሰው እጅ ያምር አሉ ,,,, " ብለው ይተርታሉ,,,, ኢቢሲ መረጃውን ሙሉን ያድርሰን አያድርሰን ባናውቅም እኛም ተመልካቾች ከጥርጣሬ ጋር አናያለን,,, ፊት ወንበር ላይ ደግሞ ወ/ ሮ ሚሚ ስብሃቱ "የተመራጭ ተደማጩ " ዛሚ ሬዲዮ ባለቤት "ሚራክል " የሆነ ሽክታ ሽክ ብለው ቁጭ ብለዋል! ! ክብ ጠረጴዛ ላይ ይሄን ጉዳይ አቅርበው ሲያብጠለጥሉት ታየኝ! !
ወ/ ሮ ፎዚያ አዋጁ ውስጥ ሚራክል መኖሩንና በሌላው አለም ካሉ ተመሳሳይ አዋጆች የተሻለ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ,,,(በአፍሪካ አንደኛ በአለም ሁለተኛ እንደማለት ነች: )
የሊቢያ አፈር ይቅለላቸውና ሙአመር ጋዳፊ ትዝ አሉኝ ,,,, አንድ ሰሞን ራሳቸው የፃፉትንና "አረንጓዴው መፅሃፍ" የሚባለውን ልክ እንደ ወ/ሮ ፎዚያ ለህዝብ እያሳዮ "አለምን መምራት የሚችል ተኣምራዊ መፅሃፍ " ብለወት ነበር,,, ያንን ፉከራ አፈር በላው!
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ,,,,
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ ! አለ ያ ቴዲ,,,, እሱ ልጅ ግን ውስጡ "ሚራክል" የሆነ ጥበብ ያለበት ልጀኮ ነው! !:)
ለማንኛውም,,,,, ማንኛውም ተቋም ባለስልጣንና የስራ ሃላፊ ለዜጎቹ መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት አዋጁ ላይ መከተቡን ነግረውናል
ለምሳሌ "ክቡር አቶ እንቶኔ እንትን ሆቴል እና እንትን ህንፃ የእርሰዎ ነው ይባላል,,,, ከየት አመጡት ብሩን " ብሎ "በአክብሮት" መጠየቅ ይቻላል እንደማለት ነው,,,:) ታዲያ አዋጁ ጨምሮ እንደሚያትተው,,,, መልሱን በአቶ እንቶኔ ፈንታ ፌዴራል ፖሊስ የመመለስ ስልጣን የለውም:):):)
እስቲ " ሚራክል" የሆነ ጊዜ ይሁንላችሁ! !

Source: Alex Abreham

No comments: