የኦሮሞ
ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመጪው ቅዳሜ በሁሉም የአገሪቷ ከተሞች የጠራውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የህዝባዊ ወያነ
ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መራሹ መንግስት ሰላማዊ ሰልፎቹን ‘ለማክሸፍ’ ምን አይነት ቅድመ ዝግጅቶች እያደረገና…. ለዕለተ
ቅዳሜ ምን አይነት እቅዶች እያወጣ እንደሚገኝ የደረሱን መረጃዎች አሉ ፤ እንደሚከተለው እናቀርባለን።
➤ ሰልፉን ለማክሸፍ እየተደረጉ የሚገኙ ቅድመ ዝግጅቶች
አንደኛ : የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይል እና አጋዚ ጦር ሰራዊት አባሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል።
ሁለተኛ : የመንግስት ሠራተኞች ቅዳሜን ስራ እንዲገቡ ተጠርተዋል። ቅዳሜ ለሚገቡ ሠራተኞች ያለወትሮ ከ100-500 ብር አበል እንደሚሰጣቸው ቃል ተገብቶላቸዋል።
ሦስተኛ : ሲቪል ለባሽ ፖሊሶች (በተለይም ኦሮምኛ ተናጋሪ ሲቪሎች) በአፋጣኝ ስብሰባዎች ተወጥረዋል።

➤ ሰልፉን ለማክሸፍ እየታቀዱ የሚገኙ ስልቶች (ተንኮሎች)
አንደኛ : በኦሮምኛ ተናጋሪ ሲቪል ለባሾች የሰላማዊ ሰልፎቹን ጥያቄዎች እና አላማዎች በተቻለ አቅም ጠልፎ (ሃይ ጃክ አድርጎ) ማስቀየር።
አንደኛ : በኦሮምኛ ተናጋሪ ሲቪል ለባሾች የሰላማዊ ሰልፎቹን ጥያቄዎች እና አላማዎች በተቻለ አቅም ጠልፎ (ሃይ ጃክ አድርጎ) ማስቀየር።
ሁለተኛ :
ሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ የሚደረጉ “መሬታችንን አትንጠቁ” መፈክሮች እና የመብት ጥያቄዎች ተከትሎ (አስታኮ) የሌሎችን መብት እና
ስሜት ሊነኩ የሚችሉ መፈክሮችን ማሰማት ብቻ ሳይሆን…. ለኢቲቪ ፕሮፖጋንዳ (ወደፊት ሊደረሱ የሚችሉ) “አስፈሪ” ዶክሜንተሪ
ፊልሞች ለመስራት የሚያመቹ ምስሎችን እና ድምፆችን መቅረጽ።
ሦስተኛ :
ሰላማዊ ሰልፎቹ በሌሎች ብሄር ተወላጆች በተለይም በአማራዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ስጋት እንዲቆጠሩ
ማረጋገጥ። (ይህን ሴራ ለጊዜው በዝርዝር መግለፁ አስፈላጊ አይደለም።)
——–
——–
ማሳሰቢያ :
በዚህ ወሳኝ ሰዓት እነዚህን ጥብቅ መረጃዎች ሰብስበን ለመለጠፍ የተገደድነው ፤ የህወሓት ዘራፊ እና ቀማኝ መራሹ ቡድን ስልጣን
ላይ ለመቆየት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የትኛውንም አይነት የሽብር ተግባር ፣ ተንኮል እና ጥቃት ከመፈፀም እንደማይቆጠብ ሰላማዊ
ሰልፈኞች ፣ የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያኖች እንዲገነዘቡ ነው።
በሌላ በኩል አሁን እየተካሄደ ያለው የመብት ፣ የነፃነት ፣ የፍትህ ፣ የእኩልነት ፣ የዲሞክራሲ ጥያቄ በሁሉም የአገር ክፍሎች ተቀጣጥሎ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ዐይኑን እና ጣቱን ህወሓት ላይ በመቀሰር የጭቆና እና ባርነት እድሜውን በአንድነት ታግሎ ሊያሳጥር የሚችለው…. የጠላቱን ስስ ብልት ሲያውቅ ብቻ ነው።
በሌላ በኩል አሁን እየተካሄደ ያለው የመብት ፣ የነፃነት ፣ የፍትህ ፣ የእኩልነት ፣ የዲሞክራሲ ጥያቄ በሁሉም የአገር ክፍሎች ተቀጣጥሎ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ዐይኑን እና ጣቱን ህወሓት ላይ በመቀሰር የጭቆና እና ባርነት እድሜውን በአንድነት ታግሎ ሊያሳጥር የሚችለው…. የጠላቱን ስስ ብልት ሲያውቅ ብቻ ነው።
በመጨረሻም
የጠላትን ደባ በማህበራዊ ድህረገፆች ቀደም ብሎ መለጠፉ እና ለህዝብ ማሳወቅ አስፈላጊነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሓት ተልካሻ ፣
አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ፕሮፖጋንዳ ተጠቂ እንዳይሆን ለመከላከል ነው።
Source: satenaw
No comments:
Post a Comment