Friday, December 18, 2015

የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሳምንታ ፓወር ማስጠንቀቂያ ሰጡ



በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሳምንታ ፓወር፣ የኢትዮጵያ መንግስት የተነሳዉን ተቃዉሞ የሚያረግብ አስቸኳይ እርምጃዎች እንዲወስድና በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ካለው የኃይል እርምጃ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀዋል። ሳማንታ ፓወር የፕሬዘዳንቱ ካቢኔ አባል የሆኑ ሲሆን፣ በዉጭ ጉዳዮሽ ዙሪያ ከኮንዶሊሳ ራይስ ያልተናነሰ በፕሬዘዳንቱ ተሰሚነት ያላቸው ባለስልጣን ናቸው።
አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ራሱንየአገር ደህነንትነ የጸረ=ሽብርተኝኘት ግብረኃይልብሎ የሚጠራው በነ ሳሞራ የኑስ የሚመራው ቡድን ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያቀርቡ እንደነበረ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም በደህንነት ሃላፊዎች ታዘው ይሁን በራሳቸው ፍቃድ ብዙ ባልታወቀ ሁኔታ፣ምህረትና ትግስ ሳናሳይ እርምጃ እንወሰዳለንብለዋል።
በዚህ መሰረት በተለያዩ ተቃዉሞ በተነሳባቸው አካባቢዎች ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል። በብዙ ቦታዎች የተነሳው ተቃዉሞ፣ እጅግ በጣም ብዙ የታጠቀ ኃይል በመሰማራቱና የጭካኔ ተግባራት በመፈጸማቸው፣ ለጊዜው ረገብ ቢልም፣ አሁንም በአንዳንድ ቦታዎች ተቃዉሞ እየተሰማ ነው። መሰረታዊ የሕዝብ የሰላም፣ የዲሞክራሲና የነጻነት ጥያቄ በአስቸኳይ እስካልተመለሰ ድረስ፣ ተረጋጉ የተባሉትም ቦታዎች እንደገና ተቃዉሟችውን ማሰማታቸው የማይቀር ነው።


No comments: