Thursday, December 24, 2015

አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይግባኝ ተጠየቀባቸው

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው ፣ጉዳያቸው ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር በላይ ሲታይ ቆይቶ ከአንዱ በስተቀር "መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ" ተብሎ ከሁለት ወራት በፊት ተወስኖላቸው የነበሩት አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡

የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች ክእሥር ከተፈቱ በኋላ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው ፣ጉዳያቸው ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር በላይ ሲታይ ቆይቶ ከአንዱ በስተቀር "መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ" ተብሎ ከሁለት  ወራት በፊት ተወስኖላቸው የነበሩት አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡
የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በአምስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ላይ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ለቃል ክርክር ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ችሎት አዟል፡፡
ፍርድ ቤቱ በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለሚከራከሩት አምስት የዞን ዘጠኝ አባላት መጥሪያውን ያወጣው ታኅሣስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ሲኾን ለቃል ክርክር ቀነ-ቀጠሮ የተያዘው ለፊታችን ታኅሣስ 20 ከጠዋቱ 2፡30 መኾኑን መጥሪያው ያትታል፡፡ መጥሪያው የደረሰው ለበፍቃዱ ኃይሉ ብቻ  መኾኑን ከጦማሪያኑ አንዱ ናትናኤል ፈለቀ ለአሜሪክ ድምጽ ተናግሯል፡፡
ዘገባውን የሠራችው ጽዮን ግርማ ነች፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይግባኝ ተጠየቀባቸው
 Source: VOA

No comments: