የወያኔ ሰራዊት አል ሻባብ የተሰኘው አለም ያወቀለትን አሸባሪ ቡድን ለመዋጋትና በሶማሊያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር በመሆን መረጋጋትን ለመፍጠር፣ ሰራዊት ማሰማራቱ ይታወቃል። ሆኖም ጋዜጠና ዳዊት ሰለሞን እንደጦመረው፣ ወአይኔ አፈሙዙን ከሽብርተኞች አንስቶ ፣ ወደ ሰላማዊ ዜጎንች ለማነጣጠር አስቧል።
ከዚህ በታችን ያለዉን ያንብቡ
መንግስት ጦሩን ከሶማሊያ ለመመለስ መንቀሳቀስ ጀምሯል - ዳዊት ሰለሞን
---
በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ውጥረት ውስጥ የገባው የኢህአዴግ መንግስት አገር ውስጥ በሚገኙ የጦር ኃይሎቹ ከህዝብ የተነሳበትን ተቃውሞ እንዳሰበው ማዳፈን ባለመቻሉና የተቃውሞው መስፋፋት ከአቅሙ ውጪ በመሆኑ ወደ ሶማሊያ ሰላም በማስከበር ስም የላካቸውን ወታደሮች ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡

የኦሮሚያ የአማራ ክልል፣የጸረ ሽብር ግብረ ኃይሉና የመንግስት ኮሚኒኬሽን የሰጧቸው መግለጫዎችም የህዝቡን ንቅናቄ የተለየ ስዕል በመቀባት ያለ የሌለ ኃይላቸውን በመጠቀም የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎች በክልሎቹ ተወላጆች በሆኑ የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ክፍፍል ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት የኢህአዴግ ከፍተኛው አመራር ቢገባውም በሶማሊያ የሚገኘው ሰራዊት እንዲመለስ መግባባት ላይ መደረሱን ምንጮች ይጠቅሳሉ፡፡
ዛሬ ምሽቱን በጦር አውሮፕላን የተሳፈሩ የሰራዊቱ አባላትም ወደ ዶዶላ እንዲያመሩ መደረጋቸውንም የአይን እማኞች ይጠቅሳሉ፡፡
No comments:
Post a Comment