Monday, December 14, 2015

ገዢው ፓርቲ ሕወሃት በስልጣን ለመቆየትም ተኩረቱን ወደ ሌላ ለማድረግ፣ በአማራውን በኦሮሞው መካከል የዘር ግጭቶች እንዲፈጠሪ እየሰራ ነው።



ገዢው ፓርቲ ሕወሃት በስልጣን ለመቆየትም ተኩረቱን ወደ ሌላ ለማድረግ፣ በአማራውን በኦሮሞው መካከል የዘር ግጭቶች እንዲፈጠሪ እየሰራ ነው። ላለፉት ሶስት ሳምንታት በኦሮሚያ በሙሉ እንቅስቃሴ መደረጉን እና ብዙ ከተሞች ከወያኔ ነጻ ሆነው እንደነበረ ይታወሳል። በዚህ ሁሉ ጊዜ በኦሮሞ ተቃዋሚዎችና በሌሎች መካከል ምንም ችገር አልተፌጥረም።

ሆኖም አሁን፣ ህወሃት ተስፋ እየቆረጠና ተቃዉሞ እየጋጠመው በመሆኑ፣ የለመደዉን የዘር ካርድ ለመጫወት እየሞከረ ነው። በዚህ መሰረት በመጠኑም ቢሆን ተሳክቶለት፣ በመራብ ሸዋ በአመያ በአማሮችና በኦሮሞዎች መካከል ግጭት ተከስቷል። ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል።
ላለፉት በርካታ አመታት ከጉሩፍርድ፣ በቤነሻንጉል፣ በከበርታ የኦሮሞ ቦታዎች በሃይል በሺሆች የሚቆጠሩ አማርኛ ተናግሪዎች ሲፈናቀሉና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምባቸው ምንም ያላለው ህወሃት፣ በወላቃይትጠገዴ አማራዎችን እያፈናቀለ ለምለም መሬታቸው እየወሰደ ያለ ህወሃት፣ በጎንደር ሰላማዊ ዜጎንች እየጨፈጨፈ ያለው ሕወሃት፣ አሁን በቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ በኩል "አማራዎች" ተቆርቋሪ ለመሆን እየሞከረ ነው።፡" የኦሮሞ አክራዊዎች በአማሮች ላይ ጥቃት አደረሱ" ሲል ለብሉምበር አስተያየት ሰጥቷል። የኦርሞ ተቃዋሚዎችን "ሽብርተኞች" ብሏቸዋል።

የኦፌኮ መሪ አቶ በቀለ ገርባ ግን፣ ሰላማዊ ዜጎንች እየጨረሱ ያሉት፣ የዘር ግጭቱ እንዲፈጠር እየቀሰቀሱና እያቀጣጠሉ ያሉት፣ የአገዛዙ ካድሬዎች መሆናቸውን ያስረዳሉ።


No comments: