Sunday, December 6, 2015

ግድ የለም ትንሿን እናደርግ - የሚሊዮኖች ድምጽ

እያንዳንዳችን የሚሊዮኖች አካል እንሆን። እውነትን፣ እኩልነትን፣ እርቅን፣ ተጠያቂነትን፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲ መብቶች መከበርን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማምጣት የተጠራ ሠላማዊና ሕገ መንግስታዎ የሆነ ንቅናቄ ነው። የነጻነት ንቅናቄ ማንም ግለሰብ ሆነ ደርጅት በባለቤትነት የሚቆጣጠረው አይደለም። የነጻነቱ ትግል ባለቤት እያንዳንዳችን ነን። ነጋሪና ቀስቃሽ ሳያስፈለግን ሁላችንም መነሳት ይኖርብናል።
የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በልጆቿ እጅ ነው እያንዳንዳችን የሥልጣን ባለቤቶችና ወሳኞች ነን ብለን ስናምንና ከኣምላክ የተሰጡንን መብቶች ለማስከበር ቆርጠን ስንነሳ፣ ያኔ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ማወጅ እንችላለን። ለሀገራችን ዘላቂ፣ ሠላማዊና ገንቢ ለውጥ ማምጣት የምንችለው፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ የፍትሕ፣ የመሬት ይዞታ መሻሻልና የነፃነት ጥያቄ፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ጥቂቶች ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎችና በጎንደር ነዋሪዎች ላይ እንዳደረጉት በአገራችን ሲያሸብሩንና ሲያስጨነቁን ዝም ልንላቸውን ልንታገሳቸው አይገባም።
የብሔረሰብ፣ የሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳያግደው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የነጻነቱ እንቅስቃሴው ኣካል እንዲሆንና የበኩሉን ኣስተዋጽኦ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
ታላቁ ምሁር ኤድመንድ በርክ (Edmund Burke) "እኔ የማደርገው ነገር ትንሽ ነው ከሚል እምነት በመነሳት ምንም ከኣለማድረግ የባሰ ስህተት የለም" ይለናል። እኛ ተራ ሰዎች ነን ብለን እናምን ይሆናል። የምናበረክተውም ነገር ትንሽ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ከሚሊዮኖች የሚገኙ ትንሽ ነገሮች፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተራ ሰዎች፣ የማይናወጥ ኃይል ይፈጥራሉ።
ትንሿን አስተዋጾ ከማድረግ እንጀመር። ከትህሳስ 1 ቀን እስከ ታህሳስ 8 የሚደረገዉን ነጻነት ተቃዉሞ ሳምንትዘመቻን ቢያንስ ለምናውቃቸው፣ አሥር ወገኖች በማሳወቅ፣ ጥሪዉን ሼር፣ ቴክስት፣ ኤስ.ኤም.ኤስ በማድረግ እንተባበር።


No comments: