ተማሪዎች ተቃዉሞ በማሰማታቸው ከኮሌጆች እየተባረሩ ነው። ወያኔ ሰላማዊ በሆነ መገድ ድምጻቸውን ያሰሙት ደብድበ፣ አሰረ፣ ገደለ። በዚያ ብቻ አልተወሰነም የዜጎች የመማር መብትን በመንፈቅ ከኮሊጆች እያባረረ ነው።
አብዝኛው የአገራችን ወጣት ከድሃ ቤተሰብ የተወለደ ነው። ተምሬ ፣ ተሻሽዬ ሥራ እይዛለሁ ብሎ የሚጠብቅ ነው። ህግ አላፈረሰም። ህግ መንግስቱ ተቃዉሞ የማሰማት መብት ሰጥቶታል። መብቱን በመጠቀም ድምጹን ሲያሰማ ግን ከትምህርት ቤት ይባረራል። የዪኒቨርሲቲ ተቁዋማትን ገለልተኝነት ያላቸውና ለተማሪዎቸው የሚቆሙ ሳይሆን የገዢው ፓርቲ ቅርንጫፎች እስከመሆን የደረሱበት ሁኔታ ነው ያለው።
የአገራችን ወጣቶች በዚህ መልክ ነገሮች እንዲጨልምባቸው እየተደረጉ የወያኔ ባለስልጣናት ግን በአመት ከ40 እስከ አምሳ ሺህ ዶላር (ወደ አንድ ሚሊዮን ብር) እየከፈሉ የነርሱን ልጆች በዉጭ አገር ያስተምራሉ።
No comments:
Post a Comment