Friday, December 25, 2015

መሬት ለሱዳን ለመስጠት በወያኔው መወሰኑ በይፋ ተገለጸ



ወያኔዎች የፖለቲካ ደርጅት መሪዎችን እና ጋዜጠኞችን እያሰሩ፣ በጎን የአገራችንን ድንበር ለሱዳን ለመስጠት መወሰናቸው ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ እየተናገሩ ነው። አቶ ኃይለማሪያም ዛሬ ፓርላማ ብለው በሚጠሩት የወያኔዎች ጉባኤ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ድንበሩ እንደሚሰመር ያረጋገጡ ሲሆን፣ ችግር እየፈጠሩ ያሉ ሱዳን ድንበር የገቡት የጎንደር ሽፍቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።
በርግጥ ፓርላማ ተብዬው ስብሰባ የኢትዮጵያ ፓርላማ ስብስብ ሳይሆን የሱዳን ፓርላማ ስብሰባ ነበር የሚመስለው። የኢትዮጵያን ጥቅም ሳይሆን ለሱዳን ጥቅም ነበር ሲንጸባረቅ የነበረው። ኢትዮጵያ ድንበር እየገቡ ወገኖቻችን በሱዳን ወታደሮች መገደላቸው ሳያንስ፣ አቶ ኃይለማሪያም እና ወያኔዎች ሱዳኖችን እንደ ሰላማዊ የጎንደርን ገበሬዎች ደግሞ እንደ ሽፍታ ለማቅረብ ሞክረዋል።
የሱዳኑ አምባሳደ ችግር "ድንበሩ የኛ ነው። የፌዴራል መንግስት ጋር ተስማምተናል፤ ያስቸገረው የአማራ ክልል መንግስት ነው " እንዳሉት ወያኔዎች ከአማራው ክልል ሕዝብ ጥቅም ዉጭ፣ ሕግ መንግስቱን እየና መሆኑን በግልጽ እያሳዩ ነው።
መሬት ለሱዳን አልሰጠንም ቢሉም፣ አቶ ኃይለማርያም መሬቱ እንደሚካላል መናገራቸው፣ አገዛዙ መሬት ለመስጠት መወሰኑን በይፋ መግለጹን የሚያሳይ ነው።


No comments: