መንግስት ህዝብ ሳያምንበት ማስተር ፕላኑን ተግባራዊ አደርጋለሁ በማለቱ ተቃውሟቸውን ያሰሙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደማይከፋፈሉና በአንድነት እንደሚቆሙ በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ፡፡ ተማሪዎቹ ዛሬ ታህሳስ 8/2008 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ለአንድነት እንቆማለን፣ አማራን እንወዳለን፣ ጉራጌን እንወዳለን፣…አንከፋፈልም…..›› ሲሉ ከሌሎች ጋር ግጭት ውስጥ እንደማይገቡና በአንድነት እንደሚቆሙ አሳውቀዋል፡፡
ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በተነሳው ሰፊ ተቃውሞ ጭንቀት ውስጥ የገባው መንግስት ተቃውሞው ‹‹የብሄር ግጭት›› እንዳስነሳ በተደጋጋሚ የገለፀ ሲሆን ይህ የመንግስት ክስ ተቃውሞውን ለማኮላሸት የተወጠነ እንደሆነ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መንግስት ተቃውሞውን ለማኮላሸት ያቀረበው ክስ መሆኑን በመግለፅ ለአንድነት እንደሚቆሙና ከሌሎች ጋር ግጭት ውስጥ እንደማይገቡ ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment