• ‹‹32 ዜጎች ተገድለዋል፣ ከመቶ በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል››
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ኢህአዴግ ህገ መንግስቱን በመጣስ የሚፈፅማቸው ህገ ወጥ እርምጃዎች ህዝብን ለከፍተኛ ችግር፣ ኢትዮጵያንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ በመሆኑ ህገ ወጥ እርምጃዎቹ በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሳስቧል፡፡ ኢህአዴግ የሚፈፅማቸውን እርምጃዎች ‹‹የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ቀምቶ መንግስት ነኝ ከሚል አካል የሚጠበቅ ነው›› ያለው መድረክ ሆኖም መዘዙ የሀገራችን፣ የህዝቦች ደህንነት፣ እኩልነት፣ እንዲሁም አንድነትን ለማይሹ አካላት ቀዳዳ የሚሰጥ በመሆኑ መድረክን በእጅጉ ያሳስበዋል ብሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በተነሳው ሰላማዊ ተቃውሞ ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ በርካቶች መገደላቸውን የገለፀው መድረክ በዜጎች ላይ የተወሰደው እርምጃም በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልፆአል፡፡ መንግስት በወሰደው እርምጃም 32 ዜጎች መገደላቸውንና ከመቶ በላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልፆአል፡፡ በሰላማዊ ተቃውሞው የተገደሉትም፡-
1. ተማሪ ካራሳ ጫላ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ
2. ተማሪ ጉቱ አበራ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ
3. ተማሪ ሚፍታህ ጁንዲ ምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ
4. ተማሪ ገዛሃኝ ኦልሂቃ የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
5. ተማሪ ደጀኔ ሰርቤሳ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ
6. ተማበቀለ ሰቦቃ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር
7. ተማሪ በቀለ ሰይፉ አዳባርጋ ወረዳ ሙገር
8. ተማሪ ሙራድ አብዲ የሃራማያ 2ኛ ደረጃ ተማሪ
9. አቶ ጫላ ተሾመ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ
10. ተማሪ አብደታ ባይሳ ምዕራብ ሸዋ ጫለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ
11. ተማሪ ዱሌ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
12. አቶ ታመነ ፀጋዬ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
13. ተማሪ ደረጀ ጋዲሳ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
14. ተማሪ ፈቃዱ ግርማ ምዕራብ ሸዋ ጨላ ወረዳ ጌዶ ከተማ
15. ተማሪ ሉጫ ገመቹ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
16. ተማሪ አያና ባንቲ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
17. ተማሪ አላዛር ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
18. አቶ ኤብሰ ቱጆ ሆሮ ጉድሩ ወረዳ ፍንጫ
19. አቶ ደበላ ጣፋ ጫንጮ ላይ
20. ወ/ሮ ዲሶ ሚኒኬሳ ህልፈታ ወረዳ
21. አቶ አበበ ቡሎ ወሊሶ ከተማ
22. አቶ ታዴ ሰፈራ አመያ ከተማ
23. አቶ ሌንጮ ሁንዴራ ወሊሶ ከተማ
24. አቶ ሰለሞን ሞገስ አማያ ወረዳ
25. አቶ ታዴ ኢንዴሳ ወንጪ ከተማ
26. አቶ አናጋው ኃይሉ ግንደበረት ወረዳ
27. ተማሪ አብደታ ለታ ግንደበረት ወረዳ
28. አቶ ባይኢሳ ገደፉ አቡና ግንደበረት ወረዳ
29. ተማሪ አስቻለው ቀርቁ ግንጪ ወረዳ
30. ተማሪ ሰይፉ ቱራ ግንጪ ወረዳ
31. ተማሪ አሸናፉ ግንጪ ወረዳ
32. አቶ ገላና ባቃና ጪቱ ከተማ መሆናቸውን በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከመቶ በላይ ዜጎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መድረክ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
2. ተማሪ ጉቱ አበራ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ
3. ተማሪ ሚፍታህ ጁንዲ ምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ
4. ተማሪ ገዛሃኝ ኦልሂቃ የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
5. ተማሪ ደጀኔ ሰርቤሳ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ
6. ተማበቀለ ሰቦቃ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር
7. ተማሪ በቀለ ሰይፉ አዳባርጋ ወረዳ ሙገር
8. ተማሪ ሙራድ አብዲ የሃራማያ 2ኛ ደረጃ ተማሪ
9. አቶ ጫላ ተሾመ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ
10. ተማሪ አብደታ ባይሳ ምዕራብ ሸዋ ጫለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ
11. ተማሪ ዱሌ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
12. አቶ ታመነ ፀጋዬ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
13. ተማሪ ደረጀ ጋዲሳ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ
14. ተማሪ ፈቃዱ ግርማ ምዕራብ ሸዋ ጨላ ወረዳ ጌዶ ከተማ
15. ተማሪ ሉጫ ገመቹ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
16. ተማሪ አያና ባንቲ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
17. ተማሪ አላዛር ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ
18. አቶ ኤብሰ ቱጆ ሆሮ ጉድሩ ወረዳ ፍንጫ
19. አቶ ደበላ ጣፋ ጫንጮ ላይ
20. ወ/ሮ ዲሶ ሚኒኬሳ ህልፈታ ወረዳ
21. አቶ አበበ ቡሎ ወሊሶ ከተማ
22. አቶ ታዴ ሰፈራ አመያ ከተማ
23. አቶ ሌንጮ ሁንዴራ ወሊሶ ከተማ
24. አቶ ሰለሞን ሞገስ አማያ ወረዳ
25. አቶ ታዴ ኢንዴሳ ወንጪ ከተማ
26. አቶ አናጋው ኃይሉ ግንደበረት ወረዳ
27. ተማሪ አብደታ ለታ ግንደበረት ወረዳ
28. አቶ ባይኢሳ ገደፉ አቡና ግንደበረት ወረዳ
29. ተማሪ አስቻለው ቀርቁ ግንጪ ወረዳ
30. ተማሪ ሰይፉ ቱራ ግንጪ ወረዳ
31. ተማሪ አሸናፉ ግንጪ ወረዳ
32. አቶ ገላና ባቃና ጪቱ ከተማ መሆናቸውን በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከመቶ በላይ ዜጎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መድረክ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
መንግስት አርሶ አደሮችን ሳያማክር እና ተገቢውን ካሳ ሳይከፍል መሬታቸውን ወደ ከተማ ለማካለል እያደረገው ባለው እንቅስቃሴ ምክንያት በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት መፈጠሩን የገለፀው መድረክ፣ ኢህአዴግ በሚፈፅመው የመሬት ቅርምት ምክንያት ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት መባባሱን ገልፆአል፡፡
ኢህአዴግ ህገ መንግስቱን እየጣሰ እየፈፀመ ካለው ህገ ወጥ ተግባር እንዲቆጠብ ያስጠነቀቀው መድረክ ለከተማ ልማት የሚወጡ እቅዶች የአርሶ አደሮችን ጥቅምና መብት ያገናዘቡ እንዲሆኑ፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዲቆም፣ በመላ ሀገሪቱ የሚኖሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ላይ የሚፈፅመው ማፈናቀል እንዲቆምና መብታቸውም እንዲጠበቅ አሳስቧል፡፡ በተጨማሪም ከተማን በማስፋፋት ሰበብ መሬትን በሊዝ ለመሸጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ አርሶ አደሩን ስጋት የከተተ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የሚይችል ካሳ ሳይከፈል ከመሬት መንቀል እንዲቆም አሳስቧል፡፡
ኢህአዴግ ህገ መንግስቱን እየጣሰ እየፈፀመ ካለው ህገ ወጥ ተግባር እንዲቆጠብ ያስጠነቀቀው መድረክ ለከተማ ልማት የሚወጡ እቅዶች የአርሶ አደሮችን ጥቅምና መብት ያገናዘቡ እንዲሆኑ፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንዲቆም፣ በመላ ሀገሪቱ የሚኖሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ላይ የሚፈፅመው ማፈናቀል እንዲቆምና መብታቸውም እንዲጠበቅ አሳስቧል፡፡ በተጨማሪም ከተማን በማስፋፋት ሰበብ መሬትን በሊዝ ለመሸጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ አርሶ አደሩን ስጋት የከተተ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የሚይችል ካሳ ሳይከፈል ከመሬት መንቀል እንዲቆም አሳስቧል፡፡
በሌላ በኩል ጎንደር ከተማ በሚገኘው እስር ቤት የተገደሉ በርካታ እስረኞችና ዜጎች ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ የሰላማዊ ዜጎችን ህይወት ያጠፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ለሟች ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይ ቋል፡፡ ‹‹በኢህአዴግ ማጭበርበርና በጉልበት በተካሄዱ ምርጫዎች የተቀማውን ህገ መንገ መንግስታዊ መብቶች ለማስከበር ሰላማዊ ትግሉን እንዲያጠናክር›› ሲልም መድረክ ለህዝብ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
Source: ነገረ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment