Thursday, December 5, 2013

የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው

የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል 

ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው


አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው።

ተከሳሾቹ  አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።

ዛሬ የፌደራሉ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤህግ በግለሰቦቹ ላይ 11 ክሶችን ነው የመሰረተባቸው ሲሆን፥ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት ማፈራትና በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አድርጎ መጠቀም የሚሉት ይጠቀሳሉ።
አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ቀደም ሲል ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ  ጋር የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል።

No comments: