Tuesday, March 22, 2016

ፍርድ ቤት ሊቀርብ የሄደው ዮናታን ተስፋዬ በሕዝብ ፊት በፖሊስ ተደ

Yonatan Regas - Satenaw
(ዘ-ሐበሻ) ላለፉት 3 ወራት በ እስር ቤት የሚገኘውና በየጊዜውም ፍርድ ቤት እየተመላለስ በፖሊስ የምርመራ አለማለቅ ሰንካላ ምክንያት ቀጠሮ ብቻ እየተለዋወጠበት የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠይቆበት ወደማረሚያ ቤት ተመለሰ::
ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበው ዮናታን ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቄ አልጨረስኩም በሚል የጠየቀው የ28 ቀናት ጭማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ለሚያዝያ 11 ተቀጥሯል:: የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት ዛሬ ዮናታን ከአራዳ ፍርድ ቤት ሲወጣ የተፈጸመበት ግፍ በጣም አሳዛኝ ነው::
እንደ አይን እማኞች ገለጻ እነዮናታንን የጫነው መኪና ከአራዳ ፍ/ቤት ግቢ ሊወጣ ሲል አንዱ ፖሊስ ከሰው ሁሉ ለይቶ የዮናታንን መስኮት መጋረጃ ሊዘጋ ይሞክራል:: ዮናታንም ለምን መጋረጃውን ትዘጋብኛለህ በሚል እምቢታውን ሲገልጽ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገባ:: በዚህ መሃል ፖሊሱ ዮናታንን በህዝብ ፊት የደበደው ቢሆንም ዮናታን መስኮቱን ባለማዘጋት ጸንቷል:: ዮናታን ቢደበደብም ራሱን ባለማስደፈሩ መኪናው ወደ ውጭ ሲወጣ በአካባቢው የነበረው ሕዝብ በጭብጨባ ለዮናታን አድናቆቱን ገልጿል::
Source: Zehabesha

No comments: