Thursday, August 6, 2015

መንግስት 71 አዳዲስ ዲፕሎማቶች ሾመ

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 29 2007
የስራ ግዜያቸው ያጠናቀቁ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዲፕሎማቶች በታወቁበት በአሁኑ ወቅት፥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሿሚዎችን ዝርዝር ማዘጋጀቱን ለኢሳት የደረሰው ሰነድ ያስረዳል ።
በሌላ በኩል የስራ ግዜያቸውን ያላጠናቀቁ በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ዲባባ አብደታ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተዋል። ምክንያቱ አልታወቀም።
ለኢሳት የደረሰው ዝርዝር እንደሚያስረዳው ሰባ አንድ ዲፕሎማቶች የተመደቡት አፍሪካ፥ መካከለኛው ምስራቅ፥ አውሮፓ፥ አሜሪካ፥ ካናዳ፥ እና አውስትራሊያ ሲሆን 8 ዲፕሎማቶች ደግሞ ከነበሩበት ወደሌላ ስፍራ እንዲዛወሩ ተደርገዋል ። ለኑሮ አደገኛና ተስማሚ ያልሆኑ ቦታዎች በሚል ዲፕሎማቶቹ የተነሱባቸው አካባቢዎች ጅቡቲ እንዲሁም በሶማሌ ሐርጌሳ ፑንት ላንድና ሞቃዲሾ የነበሩ መሆናቸው ተመልክቷል።
ከተጠቀሱት ቦታዎች የተነሱት ዲፕሎማቶች ቻይና ጣሊያን ጀርመን አሜሪካ ብራዚል ለንደንና ቶኪዮ ተዛውረዋል።
አዲስ የተሾሙትና ከአምባሳደር በታች ባሉ ቦታዎች ላይ ምደባ የወጣላቸው 71 ዲፕሎማቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪ ቤት ውስጥ ከአራት አመት እስከ ሰባት አመት ያገለገሉ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። የስራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ አዲስ አበባ ከተጠሩ ዲፕሎማቶች 6 ቱ ከሀምሌ ወር ወዲህ ስርአቱን መክዳታቸውን በሳምንቱ መጀመሪያ መግለጻችን የታወሳል።
ሆኖም ደቡብ አፍሪካ ላይ ከቀሩት ሁለቱ ዲፕሎማቶች አንዱ አቶ ኤሊያስ አወቀ በመጨረሻ ተመልሰው ሪፖርት ማድረጋቸውን የውጪ ጉዳይ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

Sourc: Esat

No comments: