Monday, April 15, 2013

ትላንት መራጭ አልባ ምርጫ ተደረገ

ትላንትየተደረገው የአካባቢና የከተማ አስተዳደር ምርጫ መራጭ አልባ እንደሆነ ተጠናቀቀ፡፡

Ethiopia-National-Election-Board-NEBE


ሚያዝያ 6 የተደረገው የተደረገው የአካባቢና የከተማ አስተዳደር ምርጫ መራጭ አልባ እንደሆነ ተጠናቀቀ፡፡
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት ምርጫ ጣቢያዎች ባዷቸውን መዋላቸው ኢህአዴግን አስደንጦታል፡፡ ከማለዳ እስከአረፋዱ ድረስ ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ የሆኑ መራጮች በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ቢታዩም ቀኑን ሙሉ ምርጫ ጣቢያዎች በዷቸውን ውለዋል፡፡ የኢህአዴግ አባላት ሆነውም ጭምር በምርጫው ያልተሳተፉ መኖራቸው በፓርቲው ውስጥ ውዝግብ የፈጠረ ሲሆን በተለያ በትግራይ እጅግ አነስተኛ ቅጥር ያለው ህዝብ በመገኘቱ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለብቴ እየዞሩ ያልመረጡ ነዋሪዎችን ያልመረጡበትን ምክንያት በመጠየቅ ያልመረጡትን ሰዎች የምርጫ ካርዳቸውን እየቀሙ መዋላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡
የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ለመምረጥ ከተመዘገበው ህዝብ መሀከል 85 በመቶው የሚሆነው ህዝብ እንደመረጠ ቢናገሩም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝብግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ለቦርዱ የተጠናቀረ መረጃ ገና እንዳልደረሰው ተናግረዋል፡፡

 

No comments: