Monday, November 27, 2017

የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይ የነበረው ዮናታን ተስፋዬ ይግባኝ ተቀባይነት አገኘ


Bilderesultat for ዮናታን ተስፋዬ


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ማለዳ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይ ዮናታን ተስፋዬ ያቀረበውን ይግባኝ ተቀብሎ ውሳኔውን ከሽብር ወደ ወንጀል ድርጊት ዝቅ አድርጎታል። 
በዚህም መሰረት ባለፈው ግንቦት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ያስተላለፈበትን የስድስት ዓመት ከስድስት ወር የእስር ፍርድ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 257 (ለ) መሰረት ወደሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝቅ አድርጎለታል።
ዮናታን በታህሳስ 2007 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የሽብር ሕጉን በመጣስ ክስ ተመስርቶበት እንደነበር ይታወሳል።
በተለይም በፌስ ቡክ ፅሁፉ የጥፋተኝነት ብያኔና የእስር ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ ይግባኝ ጠይቆ ሲከራከር ቆይቷል።

1 comment:

halalaraia said...

New Blackjack Bonus, Slots & Live Dealer Casinos | DRMCD
› casino-d › casino-d Online blackjack is one 충청북도 출장마사지 of the newest ways to enjoy real money 서귀포 출장마사지 online gambling and it 양산 출장마사지 is 통영 출장안마 among the first casinos with 김포 출장안마 live dealers.