Wednesday, May 4, 2016

ዮናታን ተስፋዬ በ”ፌስ ቡክ” ጽሁፎቹ ምክንያት በሽብርተኝነት ተከሰሰ


Yonathan Tesfaye

የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን ተስፋዬ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስመልክቶ በጻፋቸው ፌስ ቡክጽሁፎች ምክንያት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰ፡፡
ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ በእስር የቆየው ዮናታን ክስ የተመሰረተበት ዛሬ ጠዋት ወደ ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተወስደ በኋላ ነበር፡፡ በዳኛ መጓደል ምክንያት ችሎት እንኳ ያልሰየመው የከፍተኛው ፍርድቤት 19 ወንጀል ችሎት የዮናታንን ጉዳይ የተመለከተው በቢሮ ውስጥ እንደሆነ በቦታው የነበሩ እማኞች ለዋዜማ ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ ለዮናታን ክሱ ተነብቦለታል፡፡
ስድስት ገጽ የሚፈጀው የዮናታን ክስ ተከሳሹ 2001 . የወጣውን የጸረ-ሽብር ህግ አንቀጽን አራት ስር የተደነገገውን በመተላለፍ እንደተከሰሰ ያመለክታል፡፡ 15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እና ሞት የሚያስቀጣው አንቀጽ አራትየሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈጸም ማቀድ፣ መዘጋጀት፣ ማሴር፣ ማነሳሳት እና ሙከራወንጀልን የሚያስረዳ ነው፡፡
ተከሳሽ የፖለቲካ፣ አይዲዮሎጂ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት ላይ ተጽእኖ ለማሳደር፣ ህብረተሰቡን ወይም የህብረተሰቡን ክፍል ለማስፈራራት እና የሀገሪቱን መሰረታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሕገ መንግስታዊ. ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋትና ለማፈራረስበማሰብ ወንጀሉን እንደፈጸመ በክሱ ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡ ክሱ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞአመጽና ብጥብጥሲል የጠራው ሲሆን ጀማሪውም ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)” እንደሆነ በወንጀል ዝርዝሩ ላይ ያብራራል፡፡
ዮናታንንምከህዳር 24 ቀን 2008 . ጀምሮ በሚጠቀምበት ድህረ-ገፅ በተለይም በፌስ ቡክ ተጠቅሞ በሽብር ቡድኑ [ኦነግ] የተጀመረውን አመጽና ብጥብጥ ለማስቀጠልእንደሞከረ ይወነጅለዋል፡፡ ተከሳሹ በተለያየ ጊዜ የጻፋቸውን 11 የፌስ ቡክ ጽሁፎች በምሳሌነት በማንሳትም ዮናታንቀስቃሽ ጽሁፎች በመጻፍወንጀል በመፈጸሙ መከሰሱን ይገልጻል፡፡
ሀፍታሙ ቸኮለ በተባሉ የፌደራል አቃቤ ህግ አማካኝነት የቀረበው ክስ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ እንደዚሁም ኤግዚቢት እንደተካተቱበት በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡ የሰው ምስክሮች ዝርዝር በምስክሮች ጥበቃ አዋጅ መሰረት ያልተጠቀሰ መሆኑን ክሱ ያሳያል፡፡የሰነድ ማስረጃ ናቸውበሚል በአቃቤ ህግ የቀረቡት 11 ገጽ ጽሁፎች ግንተከሳሽ ከሚጠቀምበት ድህረ-ገጽየተወሰዱ እንደሆኑ በክሱ ተጽፏል፡፡ ተከሳሹ ሰጠ የተባለው 20 ገጽየእምነት ቃል አብሮ መያያዙ ተገልጿል፡፡
የሽብር ድርጊት ለመፈጸም አሲሯል በሚል በዮናታን ላይ ኤግዚቢት ተብለው የቀረቡት አንድ ኖክያ ሞባይል፣ ሁለት ሲም ካርድ እና አንድ 64GB ሜሞሪ ናቸው፡፡
ዮናታን በሰማያዊ ፓርቲ ከነበረው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት በገጻ ፍቃዱ መልቀቁን ከማሳወቁ በፊት 2007 . ምርጫ ፓርቲውን ወክሎ በቦሌ ክፍለ ከተማ ለፓርላማ የተወዳደረ ነበር፡፡

 Wazemaradio

No comments: