Friday, May 6, 2016

"ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ክስ ተመሰረተበት" ጠበቃ አመሐ መኮንን

ሚያዚያ 25 የዓለም የፕሬስ ነፃነት በተለያዩ ሀገሮች ሲከበር ኢህአዴግ "የሚዲያ ብዝሀነትን ያከበረች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል 7 ጊዜ የፕሬስ ነፃነትን ማክበሩን ገልጾ ነበር። መንግስት ይህን በዓል አከበርኩ ሲል እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ ውብሸት ተስፋዬ፣ ዳርሴማ ሶሪ፣ ዩሱፍ ጌታቸው፣ ፍቃዱ ሚርካና የመሳሰሉ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አስገብቶ ነው። ሌላው ጋዜጠኛ ጌታችው ሽፈራው በማዕከላዊ እስር ቤት ሕጉ ካስቀመጠው የምርመራ ጊዜ-ገደብ በላይ በእስር እየማቀቀ ነው።
ጠበቃው ጌታቸው ከታሰረበት ጊዜ ጀመሮ ላለፉት 4 ወራት ሊያገኙት አለቻሉም። ጠበቃ አመሐ መኮንን ደንበኛቸው ክስ ሳይመሰረትበት ለምርመራ ሕጉ ከሚፈቅደው ጊዜ በላይ በመታሰሩ "ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ" ላይ ክስ መስርተዋል
* "ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ" ወደ ማዕከሉ የገቡ ታሳሪዎች ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈጸመባቸው እስር ቤት ነው።
ከብዙ ሰቆቃዎች ውስጥ ጥቂቶቹ:-
ራቁት ማድረግ፣ ግርፋት፣ ጥፍር መንቀል፣ ዘቅዝቆ ማሰር፣ ውሀ ውስጥ መዘፍዘፍ፣ ጨለማ ቤት ውስጥ ቀናት ማቆየት፣ ቅዝቃዜ ያለባቸው ክፍሎች ውስጥ ማሰር፣ በጠባብ ክፍሎች ውስጥ በርካታ እስረኞችን ማጎር...


No comments: